የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/94 ገጽ 11
  • እንደገና አቅኚ መሆን ትችል ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንደገና አቅኚ መሆን ትችል ይሆን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአንድ ወቅት የዘወትር አቅኚ ነበርክ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • አቅኚ መሆን ትችላለህን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • በአቅኚነት አገልግሎት ተጨማሪ ወንድሞች ያስፈልጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 8/94 ገጽ 11

እንደገና አቅኚ መሆን ትችል ይሆን?

1 ባለፉት አምስት ዓመታት ብዙ ቁጥር ያላቸው የዘወትር አቅኚዎች ከዚህ መብት መውረዳቸውን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። ከእነርሱ አንዱ ነበርክን? እንደዚያ ከሆነ ይህንን መብት ለመተው ምክንያት እንደነበረህ ምንም አያጠራጥርም። ምናልባት ያልጠበቅኸውና ከአቅምህ በላይ የነበረ ነገር ገጥሞህ ይሆናል። ይህ ምክንያት እስካሁን መፍትሔ አላገኘምን? አቅኚነትህን እንድታቆም ምክንያት የሆኑህ ነገሮች የጤና እክል፣ የገንዘብ ችግር ወይም የቤተሰብ ኃላፊነቶች ከነበሩ እነዚህ ቸግሮች አሁን ተሻሽለዋልን? እንደገና ከዘወትር አቅኚነት በሚገኘው በረከት ለመደሰት የሚያስችሉህን አንዳንድ መጠነኛ ማስተካከያዎችን ልታደርግ ትችል ይሆን? እንደገና ለማመልከት አስበሃልን?

2 እንደምታውቀው የአቅኚነት አገልግሎትህ እንዲሳካልህ በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ አሠራርና ጥንቃቄ የተሞላበት ፕሮግራም ማውጣት ይጠይቅብሃል። አብዛኛውን ጊዜ ለመዝናኛ የሚሆን ሰፋ ያለ ጊዜ ባይኖርም አንድ አቅኚ መንፈሱን ለማደስ ሲል የሚያሳልፈው የተመጠነ ጊዜ በአብዛኛው ይበልጥ አርኪና የሚክስ ነው። (ምሳሌ 19:17፤ ሥራ 20:35) ራስህን በአገልግሎት በማስጠመድህ ዓለም ከሚከተለው ራስህን ብቻ ማስደሰትና መዝናናት ከሚለው የአኗኗር ፈሊጥ ትጠበቃለህ። የራስህን ጥቅም መሥዋዕት የምታደርግና የአምላክን መንግሥት የምታስቀድም ከሆነ ይሖዋ በመንፈሳዊ አብዝቶ እንደሚባርክህ ቃል ገብቷል። በይሖዋ አገልግሎት በሙሉ ልብህ የምትካፈል ከሆነ እውነተኛ ደስታና እርካታ እንደምታገኝ የተረጋገጠ ነው። — ምሳሌ 10:22፤ ቆላ. 3:23, 24

3 የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ልዩ ብቃት ላላቸው ለጥቂቶች ብቻ የተከፈተ መብት እንደሆነ ተደርጎ ሊታይ ይገባልን? በፍጹም። ራሱን ሲወስን ከገባው ስዕለት አንጻር ሁኔታዎቹ የማይፈቅዱለት ካልሆነ በስተቀር እያንዳንዱ ክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከፍተኛ ግምት ሰጥቶ ሊያስብበት ይገባል። — ማር. 12:30

4 በአሁን ወቅት ጤንነትህና ያሉብህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ኃላፊነቶች አቅኚ ሆነህ እንድታገለግል የማይፈቅዱልህ ከሆነ ይሖዋ ይህን እንደሚያውቅና ችግርህን እንደሚረዳልህ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ። ሁኔታዎቹ በፈቀዱልህ መጠን ላሳየኸው ታማኝነት ወሮታውን ይከፍልሃል። (1 ቆሮ. 4::2፤ 2 ቆሮ. 8:12) አሁን እንደገና አቅኚ ለመሆን ሁኔታዎቹ አመቺ ከሆኑልህ ግን መሪ የበላይ ተመልካቹን ቀርበህ ማመልከቻ እንዲሰጥህ ለምን አትጠይቀውም?

5 ቤተሰብህ ሊረዳህ ይችላልን? ምናልባት አቅኚነትን ያቆምከው የቤተሰብ ኃላፊነቶችህን ለመወጣት ስትል ይሆናል። ወደ አቅኚነቱ ሥራ ለመመለስ እንድትችል ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ኃላፊነቶችህን ሊጋሩህ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋልን? አንዳንዶች አቅኚነታቸውን እንደገና ለመጀመር የሚያስፈልጋቸው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያስችል ጥቂት ድጋፍ ብቻ ነው።

6 ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ቀና ትብብርና ተጨማሪ ጥረት ካሳዩ ይህን ማድረግ ቀላል ሊሆን ይችላል። እርዳታው በገንዘብ ወይም መጓጓዣ በማቅረብና አብሮ በአገልግሎት ለመሰማራት መደበኛ ቀጠሮ በመያዝም ጭምር ሊደረግ ይችል ይሆናል። እርዳታ መስጠት የሚችሉባቸው ሌሎች መንገዶችም ይኖራሉ። እንደገና ወደዚህ የአገልገሎት መብት ለመድረስ ሁኔታዎቹ የማይፈቅዱልህ ከሆነ ከቤተሰቡ አባላት መካከል ይህን ማድረግ ለሚችል ለአንዱ እነዚህን እርዳታዎች መስጠት ይቻል ይሆናል።

7 በዚህ ጉዳይ ላይ በቤተሰብ መልክ ሆናችሁ ለምን አትወያዩም? በአንድነት የሚሠራ የቤተሰብ ፕሮጄክት ካደረጋችሁት ከቤተሰባችሁ አንዱ አቅኚ ለመሆን ያለው ተስፋ የተሻለ ይሆናል። በዚህ መልክ ከቤተሰቡ አንዱ አቅኚ ከሆነ መላው ቤተሰብ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ሊሰማው ይችላል። ይህም ትክክል ነው። እንደዚህ ያለው የሰጪነት መንፈስ በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ የሚሰጠውን የመንግሥት ምሥክርነት ከፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም በመንፈሳዊ ያቀራርባል። — ሉቃስ 6:38፤ ፊል. 2:2-4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ