የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/95 ገጽ 3
  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 6/95 ገጽ 3

ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

1 ይሖዋ በጊዜ በአግባቡ የሚጠቀም አምላክ ነው። እኛም በጊዜ ረገድ ጠንቃቆች አንድንሆን ይፈልጋል። በድርጅቱ አማካኝነት ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀምበት እርዳታ ያቀርብልናል። ሁልጊዜ ‘የጌታ ሥራ የበዛልን’ እንድንሆን ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል። (1 ቆሮ. 15:58) በዚህ መንገድ በይሖዋ አገልግሎት ይበልጥ የተዋጣልን መሆን እንች ላለን።

2 ሁላችንም በሳምንት ውስጥ እኩል የሆነ ማለትም 168 ሰዓት አለን። ታዲያ በጊዜያችን ደህና አድርገን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? ጊዜን የምንመለከተው ይሖዋ በሚመለከትበት መንገድ ነውን? አላስፈላጊ በሆኑ እንቅስቃሴዎች እንባክናለንን?

3 በጥሩ ሁኔታ የተደራጀን መሆን አስፈላጊ ነው። ብዙዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ሥራዎች በጽሑፍ ለማስፈር ይጥራሉ። እያንዳንዱ ጉዳይ እንደ አንገብጋቢነቱ በቅደም ተከተል ይቀመጣል። አንገብጋቢነቱ እንዴት ሊወሰን ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው ‘በድካሙ ደስ’ ሊለው እንደሚገባ ይናገራል። (መክ. 3:13) አንዳንድ ሥራዎች ከሌሎች የተሻሉ ውጤቶችን ያስገኛሉ። እያንዳንዱ ሥራ የሚያመጣውን ውጤቶች አመዛዝን። ሥራውን አከናውኖ መጨረሱ ጎላ ያሉ ጥቅሞች ያስገኛልን? የምትደክምለት ሥራ ኋላ ‘ደስታ’ ያስገኝልሃልን? ካልሆነ ሥራው ቅድሚያ የሚሰጠው ላይሆን ይችላል።

4 በአገልግሎታችን፦ ሌሎች ለመስክ ስምሪት ስብሰባ ልክ በሰዓቱ ሲደርሱ፣ የሚሰጡትን ትምህርቶች ልብ ብለው ሲያዳምጡና ስብሰባው ልክ እንዳለቀ ወደ ክልላቸው ሲሄዱ እናደንቃለን። ሰው ከመጠበቅ ይልቅ በስብከት ሥራ መወጠር እንፈልጋልን። ጳውሎስ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” ብሎ ሲጽፍ በሥርዓት የመመላለስ አስፈላጊነት በግልጽ ተሰምቶት ነበር።— 1 ቆሮ. 14:40

5 መስክ አገልግሎት ወጥተን ውድ የሆነውን ጊዜ በሻይ እረፍት ልናቃጥል እንችላለን። ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ትንሽ እረፍት ማድረጉ ጉልበታችንን ከማደሱም በተጨማሪ አገልግሎታችንን እንድንቀጥል ይረዳናል። ቢሆንም ብዙዎች ከወንድሞች ጋር አብረው በመሆን ሻይ ቡና ከማለት ይልቅ ለሰዎች በመመሥከር እንደተጠመዱ መቀጠልን መርጠዋል። ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል።

6 መጽሐፍ ቅዱስ “ሽመላዎች እንኳ” ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚፈልሱበትን “ጊዜ ያውቃሉ፤” እንዲሁም ጉንዳን ለክረምት ዝግጁ መሆን እንድትችል “መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች” በማለት ይናገራል። (ኤር. 8:7 የ1980 ትርጉም፤ ምሳሌ 6:6–8) ጊዜን በጥበብ መጠቀም የምንችልበት ቁልፍ እዚህ ላይ ይገኛል። እኛም ‘ፕሮግራማችንን ማወቅ’ አለብን። እጅግም ግትር ሳንሆን በጊዜያችን በአግባቡ መጠቀም አለብን። ምን እንደምንሠራ ብቻ ሳይሆን መቼ መሠራት እንደሚያስፈልገውም ማወቅ ያስፈልገናል። ወደፊት ፕሮግራማችን ሊስተጓጎል ስለሚችል በምናወጣው ፕሮግራም ላይ መጠባበቂያ ጊዜ በመመደብ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ ማውጣትን ልምዳችን ማድረግ አለብን። በተጨማሪም ለስብሰባዎች፣ ለመስክ አገልግሎትና ለሌሎች ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ዝግጅት ማድረግን ለመሳሰሉ ይበልጥ አንገብጋቢ ለሆኑ ነገሮች ጊዜ ማግኘት አንድንችል አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ለማሳጠር ፈቃደኛ መሆን አለብን።

7 “ለሁሉ ዘመን አለው” ብሎ የሚያስተምረንን ሰማያዊ አባታችንን ይሖዋ አምላክን ለመምሰል እንፈልጋለን። (መክ. 3:1) በጊዜያችን በጥበብ በመጠቀም ‘አገልግሎታ ችንን ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም እንችላለን።’— 2 ጢሞ. 4:5 አዓት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ