የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/98 ገጽ 3-5
  • በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 ያም ሆኖ ግን ሳናውቅ አንዳንዶችን ከመኝታቸው ልንቀሰቅሳቸው ወይም ልንረብሻቸው እንችል ይሆናል። ምናልባትም ሰውዬው በጣም ሊበሳጭ ወይም ሊቆጣ ይችላል። ምን ማድረግ ይኖርብናል? ምሳሌ 17:27 “መንፈሱ ቀዝቃዛ የሆነ ሰው አስተዋይ ነው” የሚል ምክር ይሰጠናል። ስለ አገልግሎታችን ይቅርታ ባንጠይቅም አመቺ ባልሆነ ጊዜ ወደ እርሱ በመሄዳችን እንዳዘንን ልንገልጽ እንችላለን። ሌላ ይበልጥ አመቺ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ በትሕትና ጠይቀን በዚያ ጊዜ ልናነጋግረው እንደምንመጣ ልንገልጽ እንችላለን። ልባዊ የአሳቢነት ስሜታችንን በለዘበ አነጋገር መግለጻችን ብዙውን ጊዜ ሰውዬውን ለማረጋጋት ያስችላል። (ምሳሌ 15:1) አንድ የቤት ባለቤት ሁልጊዜ በሌሊት ፈረቃ የሚሠራ መሆኑን ከነገረን ወደፊት ወደዚያ ቤት የሚሄዱ አስፋፊዎች አመቺ በሆነ ጊዜ ሊጠይቁት ይችሉ ዘንድ ከአገልግሎት ክልል ካርዱ ጋር ማስታወሻ መያያዝ ይኖርበታል።
  • 12 የአገልግሎት ክልላችንን አጣርተን ለመሸፈን ስንጥርም አስተዋይነት ማሳየት አስፈላጊ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሄድ ብዙ ሰዎችን ቤታቸው ካላገኘናቸው የመዳንን መልእክት ልናካፍላቸው እንችል ዘንድ እነርሱን ለማግኘት ተጨማሪ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። (ሮሜ 10:13) አንዳንድ ጊዜ አስፋፊዎች ሰዎቹን እቤታቸው ለማግኘት ሲሉ በቀን ውስጥ ደጋግመው ወደ አንዱ ቤት ይሄዳሉ። እግር ማብዛታቸውን ጎረቤቶች ያስተውላሉ። የይሖዋ ምሥክሮች ‘አሁንም አሁንም እየመጡብን ነው’ የሚል ስሜት ያድርባቸው ይሆናል። ይህንን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው?
  • 13 ማስተዋል ይኑራችሁ። ቤታቸው ያልተገኙ ሰዎችን ለመጠየቅ ተመልሰን በምንሄድበት ጊዜ አንድ ሰው በቤት ውስጥ እንዳለ የሚጠቁም ነገር አለ? ምሽቱንም ጨምሮ በቀኑ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ሙከራዎች ተደርገው ሰውየውን ማግኘት ካልተቻለ ሰውዬውን በስልክ ማግኘት ይቻል ይሆናል። አለዚያም በተለይ ክልሉ በበቂ ሁኔታ ተደጋግሞ የተሠራበት ከሆነ አንድ ትራክት ወይም የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ቀስ ብለን በቤቱ በር በኩል አሽሉከን ልናስገባለት እንችል ይሆናል። ምናልባትም በሚቀጥለው ጊዜ የአገልግሎት ክልሉ ሲሸፈን ሰውዬው ይገኝ ይሆናል።
  • 14 የቤቱ ባለቤት ታምሞ ወይም ለመጥፎ የአየር ጠባይ ተጋልጦ እያለ ውይይቱን ለረጅም ሰዓት እንዲቀጥል ማድረጉ አግባብ አይደለም። ወደ ቤት ውስጥ እንድንገባ ስንጋበዝ የቤቱን ወለል እንዳናቆሽሽ መጠንቀቅ ይኖርብናል። በአፓርታማዎች ውስጥ በምናገለግልበት ጊዜ ተከራዮችን የሚረብሽና የይሖዋ ምሥክሮች መጡ የሚያሰኝ ድምፅ ላለመፍጠር ቀስ ብላችሁ ተነጋገሩ።
  • 15 ሥርዓታማ ሁኑ፤ የሚያስከብር ሁኔታ ይኑራችሁ፦ በጥሩ ሁኔታ ከተደራጀን በአገልግሎት ክልል ውስጥ በብዛት ተከማችተን እንዳንታይ ማድረግ እንችላለን። አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ቤታቸው ፊት ለፊት በርካታ መኪናዎች ተደርድረው ወይም ብዙ አስፋፊዎች ተከማችተው ሲያዩ ፍርሃት ያድርባቸዋል። የመኖሪያ አካባቢዎችን “እንደ ወረርን” የሚያስመስል ሁኔታ እንዲፈጠር አንፈልግም። የአገልግሎት ክልሉን መሸፈን የምንችልበትን መንገድ በመስክ ስምሪት ስብሰባ ላይ ማዘጋጀቱ የተሻለ ይሆናል። እንደ አንድ ቤተሰብ ያሉ ትናንሽ ቡድኖች ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ የቤቱን ባለቤቶች ሥጋት የሚቀንስ ሲሆን የአገልግሎት ክልሉንም ለመሸፈን የሚደረገውን ቅንጅት ሥራ የሚያቀል ይሆናል።
  • 16 ሥርዓታማነት ወላጆች በአገልግሎት ክልል ውስጥ ሲሠሩ ልጆቻቸው ጥሩ ጠባይ እንዲኖራቸው መከታተልንም የሚጠይቅ ነው። ልጆች ከትላልቆች ጋር ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ የታረመ ጠባይ ማሳየት ይኖርባቸዋል። ልጆች የነዋሪዎቹን ወይም በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎችን አላስፈላጊ ትኩረት በሚስብ መንገድ እንዲጫወቱ ወይም ወዲያና ወዲህ እንዲሯሯጡ ሊፈቀድላቸው አይገባም።
  • 17 በሻይ ረፍት ረገድም ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል። የሰኔ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ እንዲህ ብሎ ነበር:- “መስክ አገልግሎት ወጥተን ውድ የሆነውን ጊዜ በሻይ እረፍት ልናቃጥል እንችላለን። ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ትንሽ እረፍት ማድረጉ ጉልበታችንን ከማደሱም በተጨማሪ አገልግሎታችንን እንድንቀጥል ይረዳናል። ቢሆንም ብዙዎቹ ከወንድሞች ጋር አብረው በመሆን ሻይ ቡና ከማለት ይልቅ ለሰዎች በመመሥከር እንደተጠመዱ መቀጠልን መርጠዋል።”
  • 18 ብዙዎች ሰዎችን ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ማለትም በመንገድ ላይ፣ በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እንዲሁም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው በሌሎች ቦታዎች በመሄዳቸው ግሩም ውጤቶች አግኝተዋል። በእነዚህ አካባቢዎችም ቢሆን በቃላችን ብቻ ሳይሆን በምናሳየው ምክንያታዊነትም ግሩም ምሥክርነት መስጠት እንፈልጋለን። በእያንዳንዱ ጉባኤ ውስጥ ያሉ አስፋፊዎች የአገልግሎት ክልል ወሰናቸውን ማክበር የሚኖርባቸው ሲሆን በንግድ አካባቢዎች ወይም በሥራ ቦታዎች አካባቢ የሚጓዙ እግረኞችን አሁንም አሁንም እንዳያስቆሟቸው በአንድ መንገድ ላይ፣ አደባባይ ላይ ወይም መናፈሻ ውስጥ ስንት አስፋፊዎች እንዳሉ ማስተዋል ይኖርባቸዋል። ከመንገድ ወደ መንገድ ስናገለግልም ቢሆን ፍሬያማ የመሆን ግብ በመያዝ ትኩረታችን በአገልግሎቱ ላይ እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል። ስለ ግል ጉዳያችን በማውራት መጠመድ አንፈልግም። ባብዛኛው ሲታይ ልናነጋግራቸው የምንችል ብዙ ሰዎች ስለምናገኝ ስለ ምሥራቹ ሳንናገር ብዙ ደቂቃዎች እንድናሳልፍ የሚያስገድድ ሁኔታ አይኖርም። አገልግሎታችንን ሥርዓታማና ክብር ባለው መንገድ ለማከናወን እንድንችል በጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል ሌላ ጉባኤ ለመርዳት የምንችልበት ዝግጅት እስካልተደረገልን ድረስ በጉባኤያችን የአገልግሎት ክልል ውስጥ ብቻ መሥራት ይኖርብናል።—ከ2 ቆሮንቶስ 10:13–15 ጋር አወዳድር። (የ1980 ትርጉም)
  • 19 ለሕዝብ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ ብዙ አካባቢዎች ያሏቸው ጉባኤዎች እነዚሁኑ ቦታዎች በአገልግሎት ክልል መልክ ሸንሽነዋቸዋል። ከዚያም የአገልግሎት ክልል ካርታው ለአንድ አስፋፊ ወይም ለአንድ የአስፋፊዎች ቡድን ይሰጣል። ይህም ክልሉን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመሸፈን ከማስቻሉም በላይ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” ከሚለው የ1 ቆሮንቶስ 14:40 መሠረታዊ ሥርዓት ጋር በሚስማማ መንገድ በርካታ አስፋፊዎች በአንድ አካባቢ እንዳይሠማሩ ለማድረግ ይረዳል።
  • 21 በ1 ቆሮንቶስ 9:26 ላይ ጳውሎስ “ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፣ ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም” ሲል ተናግሯል። የጳውሎስን ምሳሌ በመኮረጅ የእኛም ቁርጥ ውሳኔ ውጤታማና ፍሬያማ አገልግሎት ማከናወን ነው። ዛሬ ያለው የይሖዋ ‘የአንበጣ ሠራዊት’ ክፍል በመሆን በምሥክርነቱ ሥራ በቅንዓት ስለምንካፈል በክልላችን ውስጥ ላሉት ሰዎች የመዳንን መልእክት ስናደርስ ክርስቲያናዊ ምክንያታዊነትና ማስተዋል ይኑረን።
  • ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • የግል የአገልግሎት ክልል ቢኖርህ ትጠቀማለህ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • በአገልግሎታችሁ ወርቃማውን ሕግ ተግባራዊ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 11/98 ገጽ 3-5

በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ

1 ሰማዩ ይጨልማል፣ ጆሮ ጭው የሚያደርግ አስፈሪ ድምፅ መጠኑ እየጨመረ ይመጣል። እንደ ጭስ ያለ ዳመና ከሰማይ መውረድ ይጀምራል። ይህ ምንድን ነው? በሚልዮን የሚቆጠሩ አንበጦችን ያቀፈ ሠራዊት በምድሪቱ ላይ የከፋ ውድመት ለማስከተል እየመጣ ነው! ይህ ነቢዩ ኢዩኤል የገለጸው ትዕይንት ዛሬ የአምላክ ቅቡዓን አገልጋዮችና የእነርሱ ጓደኞች የሆኑት እጅግ ብዙ ሰዎች በሚያከናውኑት የስብከት ሥራ አማካኝነት ፍጻሜውን እያገኘ ነው።

2 የግንቦት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11 አንቀጽ 19 ላይ እንዲህ ብሎ ነበር:- “የዘመናችን የአምላክ የአንበጣ ሠራዊት በሕዝበ ክርስትና ‘ከተማ’ ውስጥ የተጣራ ምሥክርነት ሰጥተዋል። (ኢዩ. 2:9) . . . አሁንም ቢሆን ማንኛውንም ዓይነት እንቅፋት እየተወጡ በሚልዩን ወደሚቆጠሩ ቤቶች ይሄዳሉ፣ ሰዎችን በመንገድ ላይ፣ በስልክና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በማነጋገር የይሖዋን መልእክት እያወጁ ነው።” በዚህ አምላክ በሰጠን ሥራ ውስጥ መካፈል ታላቅ መብት አይደለምን?

3 ራሳቸውን ብቻ ከሚመግቡት አንበጦች በተለየ መልኩ እኛ የይሖዋ አገልጋዮች ስለምንሰብክላቸው ሰዎች ሕይወት በጥልቅ እናስባለን። ሌሎች ሰዎች በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ክብራማ እውነት እንዲማሩና ወደ ዘላለም መዳን የሚያደርሳቸውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲነሳሱ መርዳት እንፈልጋለን። (ዮሐ. 17:3፤ 1 ጢሞ. 4:16) በመሆኑም አገልግሎታችንን የምናከናውንበት መንገድ ውጤታማ እንዲሆን እንፈልጋለን። የትኛውንም የስብከት ዘርፍ እንጠቀም የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ በሚችል መንገድና ጊዜ እያከናወን ስለመሆናችን ልናስብ ይገባናል። ‘የዚህ ዓለም መልክ ተለዋዋጭ’ እንደመሆኑ የተቻለንን ያህል ውጤታማ መሆን እንችል ዘንድ የሚገጥሙንን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ለማሸነፍ ዘዴያችንንና አቀራረባችንን መገምገማችን ተገቢ ይሆናል።—1 ቆሮ. 7:31 NW

4 ሰዎችን በብዙ መንገዶች ለማግኘት የምንጥር ቢሆንም ከቤት ወደ ቤት የምናደርገው ስብከት አሁንም የአገልግሎታችን ዋነኛ ምሰሶ ነው። ከቤት ወደ ቤት በምትሄዱበት ጊዜ በአንዳንድ ክልሎች የሚኖሩ ሰዎች ቤታቸው የማይኖሩበት ወይም ገና ከእንቅልፋቸው ያልተነሱበት ሁኔታ ያጋጥማችኋል? የምሥራቹን መልእክት ልታካፍሏቸው አለመቻላችሁ ምንኛ የሚያሳዝን ነው! ይህን ተፈታታኝ ሁኔታ መወጣት የምትችሉት እንዴት ነው?

5 ከሁኔታው ጋር ራሳችሁን የምታስተካክሉና ምክንያታዊ ሁኑ፦ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በእስራኤል ይኖሩ የነበሩ ዓሣ አጥማጆች ዓሦችን የሚያጠምዱት ከመሸ በኋላ ነበር። ለምን? ይህ ጊዜ ለእነርሱ አመቺ ባይሆንም ብዙ ዓሣ ለማጥመድ የሚያስችላቸው ከሁሉ የተሻለው ጊዜ ግን ነበር። እጅግ ፍሬያማ የሚሆኑበት ጊዜ ነበር። ይህን ልማዳቸውን በሚመለከት የሰኔ 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ ሐሳብ ሲሰጥ እንዲህ ብሏል:- “እኛም የክልላችንን ሁኔታ ማጥናትና አብዛኞቹ ሰዎች እቤታቸው በሚገኙበትና ምሥራቹን ለመስማት በሚችሉበት ጊዜ ዓሣ የማጥመድ ሥራችንን ማከናወን ይኖርብናል።” በብዙ ከተማ ቀመስ ማኅበረሰቦችና የመኖሪያ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ማኅበራዊ ሁኔታ በጥንቃቄ በመመርመር መገንዘብ እንደተቻለው ቅዳሜ ወይም እሁድ ጠዋት ላይ ስንሄድ ቤታቸው የምናገኛቸው ቢሆንም በአጠቃላይ ሲታይ ግን በዚህ ጊዜ ለምናደርገው ውይይት የተቀባይነት ዝንባሌ አያሳዩም። ይህ ሁኔታ በእናንተ አካባቢም የሚታይ ከሆነ ጠዋት ረፈድ አድርጋችሁ ወይም ደግሞ ከሰዓት በኋላ ለመሄድ ትችሉ ይሆን? ይህ የአገልግሎታችንን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚ ከመሆኑም በላይ ለጎረቤቶቻችን አሳቢነት የምናሳይበት ግሩም መንገድ ነው። ይህ ደግሞ የእውነተኛ ክርስቲያናዊ ፍቅር መግለጫ ነው።—ማቴ. 7:12

6 በፊልጵስዩስ 4:5 [NW] ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ምክንያታዊነታችን ለሰው ሁሉ ግልጽ ሆኖ እንዲታይ’ አሳስቦናል። የስብከት ተልዕኳችንን በቅንዓትና በግለት ስንፈጽም ከዚህ በመንፈስ አነሳሽነት የተሰጠ መመሪያ ጋር በሚስማማ መንገድ በምንጠቀምባቸው ዘዴዎች ረገድ ሚዛናዊነትንና ምክንያታዊነትን ማሳየት ይኖርብናል። ይህ ማለት ግን ‘በሕዝብ ፊት እንዲሁም ከቤት ወደ ቤት ማስተማርን’ እንተዋለን ማለት ሳይሆን ከቤት ወደ ቤት የምናደርገውን አገልግሎት አመቺ በሆነና ፍሬ በሚያስገኝ ወቅት ማከናወን እንፈልጋለን ማለታችን ነው። (ሥራ 20:20) በመጀመሪያው መቶ ዘመን በእስራኤል እንደ ነበሩት ዓሣ አጥማጆች ይበልጥ የሚያሳስበን ለራሳችን አመቺ ሆኖ በምናገኘው ጊዜ ‘ማጥመዳችን’ ሳይሆን ይበልጥ ውጤታማ መሆን በምንችልበት ጊዜ ማጥመዳችን ነው።

7 ታዲያ ምን ዓይነት ማስተካከያዎችን ማድረግ ይቻላል? ብዙውን ጊዜ ቅዳሜና እሁድ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች የሚካሄዱት ጠዋት በ2:30 ወይም በ3:00 ላይ ነው። ከዚያ በኋላ ቡድኑ ወዲያውኑ ወደ ክልሉ ገብቶ ከቤት ወደ ቤት መሥራት ይጀምራል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የሽማግሌዎች አካላት ወንድሞች ወደ መኖሪያ ክልሎች ገብተው ከቤት ወደ ቤት መሥራት ከመጀመራቸው በፊት ከመንገድ ወደ መንገድ ማገልገልን፣ በገበያ ክልሎች መሥራትን ወይም ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግን በመሳሰሉት ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች እንዲሳተፉ ዝግጅት አድርገዋል። ሌሎች ጉባኤዎች ደግሞ የመስክ ስምሪት የሚያደርጉበትን ጊዜ ረፈድ አድርገውታል። ከዚያ በኋላ ወንድሞች ቀጥታ ወደ ክልሉ ሄደው ከቤት ወደ ቤት በማንኳኳት እስከ ሰባትና ስምንት ሰዓት ድረስ በአገልግሎት ላይ ይቆያሉ። በአንዳንድ የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ ከጠዋት ይልቅ ሰባትና ስምንት ሰዓት ላይ የመስክ ስምሪት ስብሰባ ማድረጉ ይበልጥ አመቺ ሊሆን ይችላል። እንዲህ ያለው ማስተካከያ ከቤት ወደ ቤት የሚደረገው አገልግሎት ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን ጥሩ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይችላል።

8 አስተዋዮችና ዘዴኞች ሁኑ፦ ከቤት ወደ ቤት ሄደን የምናገኛቸው ሰዎች ለመልእክታችን የሚሰጡት ምላሽ የተለያየ ነው። አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ተቀባዮች ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ግዴለሽ ናቸው። ጥቂቶች ደግሞ ተከራካሪዎች ወይም ጠበኞች ሊሆኑ ይችላሉ። ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር የተባለው መጽሐፍ በገጽ 7 ላይ ተከራካሪ ወይም ጠበኛ የሆኑ ሰዎች በሚገጥሙን ጊዜ ‘ለእውነት አክብሮት የሌላቸውን ሰዎች “በክርክር የመርታት”’ ዓላማ እንደሌለን ያሳስበናል። የቤቱ ባለቤት ጥላቻ ያለው ከሆነ ትተነው መሄዳችን ከሁሉ የተሻለ ይሆናል። ሰዎች እንዲያነጋግሩን ወይም የእኛን አመለካከት እንዲቀበሉ በመጎትጎት የጥላቻ መንፈስ እንዲያድርባቸው ማድረግ አይኖርብንም። ሰዎች መልእክታችንን እንዲቀበሉ አናስገድዳቸውም። ይህን ማድረግ ምክንያታዊ ካለመሆኑም ሌላ በሌሎች ምሥክሮችና በጠቅላላው በሥራው ላይ ችግር እንዲፈጠር ልናደርግ እንችላለን።

9 በአንድ የአገልግሎት ክልል ውስጥ መሥራት ከመጀመራችን በፊት ተመልሰን እንዳንሄድበት የጠየቀ ሰው መኖር አለመኖሩን የሚገልጽ አስተያየት ሰፍሮበት እንደሆነ የአገልግሎት ክልል ካርዱን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። የተጠቆሙ አድራሻዎች ካሉ በዚያ አካባቢ የሚሠራ እያንዳንዱ አስፋፊ የትኛውን ቤት ማንኳኳት እንደሌለበት ሊነገረው ይገባል። ከአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ መመሪያ ካላገኘ በስተቀር ማንኛውም አስፋፊ በራሱ ተነሳስቶ እንዲህ ያሉትን ቤቶች ማንኳኳት አይኖርበትም።—በሰኔ 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።

10 ከቤት ወደ ቤት በምንሠራበት ጊዜ አስተዋዮች በመሆን ውጤታማነታችንን ማሳደግ እንችላለን። ወደ አንድ ቤት ስትሄዱ ሁኔታውን አስተውሉ። መጋረጃዎቹ ወይም መስኮቶቹ ተዘግተዋል? ምንም የሚሰማ ድምፅ የለምን? ይህ ምናልባት ሰዎቹ መተኛታቸውን የሚጠቁም ሊሆን ይችላል። ቆየት ብለን ብንመጣ ከቤቱ ባለቤት ጋር ይበልጥ ፍሬያማ የሆነ ውይይት ማድረግ እንችል ይሆናል። ምናልባትም የቤቱን ቁጥር በማስታወሻችን ላይ ይዘን ለጊዜው ቤቱን ማለፍ የተሻለ ሆኖ እናገኘው ይሆናል። ከክልሉ ከመውጣታችሁ በፊት ቤቱን እንደገና ልትጎበኙት ወይም በሌላ ሰዓት ተመልሳችሁ ለመምጣት ማስታወሻችሁ ላይ ልታሰፍሩት ትችላላችሁ።

11 ያም ሆኖ ግን ሳናውቅ አንዳንዶችን ከመኝታቸው ልንቀሰቅሳቸው ወይም ልንረብሻቸው እንችል ይሆናል። ምናልባትም ሰውዬው በጣም ሊበሳጭ ወይም ሊቆጣ ይችላል። ምን ማድረግ ይኖርብናል? ምሳሌ 17:27 “መንፈሱ ቀዝቃዛ የሆነ ሰው አስተዋይ ነው” የሚል ምክር ይሰጠናል። ስለ አገልግሎታችን ይቅርታ ባንጠይቅም አመቺ ባልሆነ ጊዜ ወደ እርሱ በመሄዳችን እንዳዘንን ልንገልጽ እንችላለን። ሌላ ይበልጥ አመቺ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ በትሕትና ጠይቀን በዚያ ጊዜ ልናነጋግረው እንደምንመጣ ልንገልጽ እንችላለን። ልባዊ የአሳቢነት ስሜታችንን በለዘበ አነጋገር መግለጻችን ብዙውን ጊዜ ሰውዬውን ለማረጋጋት ያስችላል። (ምሳሌ 15:1) አንድ የቤት ባለቤት ሁልጊዜ በሌሊት ፈረቃ የሚሠራ መሆኑን ከነገረን ወደፊት ወደዚያ ቤት የሚሄዱ አስፋፊዎች አመቺ በሆነ ጊዜ ሊጠይቁት ይችሉ ዘንድ ከአገልግሎት ክልል ካርዱ ጋር ማስታወሻ መያያዝ ይኖርበታል።

12 የአገልግሎት ክልላችንን አጣርተን ለመሸፈን ስንጥርም አስተዋይነት ማሳየት አስፈላጊ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሄድ ብዙ ሰዎችን ቤታቸው ካላገኘናቸው የመዳንን መልእክት ልናካፍላቸው እንችል ዘንድ እነርሱን ለማግኘት ተጨማሪ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። (ሮሜ 10:13) አንዳንድ ጊዜ አስፋፊዎች ሰዎቹን እቤታቸው ለማግኘት ሲሉ በቀን ውስጥ ደጋግመው ወደ አንዱ ቤት ይሄዳሉ። እግር ማብዛታቸውን ጎረቤቶች ያስተውላሉ። የይሖዋ ምሥክሮች ‘አሁንም አሁንም እየመጡብን ነው’ የሚል ስሜት ያድርባቸው ይሆናል። ይህንን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

13 ማስተዋል ይኑራችሁ። ቤታቸው ያልተገኙ ሰዎችን ለመጠየቅ ተመልሰን በምንሄድበት ጊዜ አንድ ሰው በቤት ውስጥ እንዳለ የሚጠቁም ነገር አለ? ምሽቱንም ጨምሮ በቀኑ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ሙከራዎች ተደርገው ሰውየውን ማግኘት ካልተቻለ ሰውዬውን በስልክ ማግኘት ይቻል ይሆናል። አለዚያም በተለይ ክልሉ በበቂ ሁኔታ ተደጋግሞ የተሠራበት ከሆነ አንድ ትራክት ወይም የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ቀስ ብለን በቤቱ በር በኩል አሽሉከን ልናስገባለት እንችል ይሆናል። ምናልባትም በሚቀጥለው ጊዜ የአገልግሎት ክልሉ ሲሸፈን ሰውዬው ይገኝ ይሆናል።

14 የቤቱ ባለቤት ታምሞ ወይም ለመጥፎ የአየር ጠባይ ተጋልጦ እያለ ውይይቱን ለረጅም ሰዓት እንዲቀጥል ማድረጉ አግባብ አይደለም። ወደ ቤት ውስጥ እንድንገባ ስንጋበዝ የቤቱን ወለል እንዳናቆሽሽ መጠንቀቅ ይኖርብናል። በአፓርታማዎች ውስጥ በምናገለግልበት ጊዜ ተከራዮችን የሚረብሽና የይሖዋ ምሥክሮች መጡ የሚያሰኝ ድምፅ ላለመፍጠር ቀስ ብላችሁ ተነጋገሩ።

15 ሥርዓታማ ሁኑ፤ የሚያስከብር ሁኔታ ይኑራችሁ፦ በጥሩ ሁኔታ ከተደራጀን በአገልግሎት ክልል ውስጥ በብዛት ተከማችተን እንዳንታይ ማድረግ እንችላለን። አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ቤታቸው ፊት ለፊት በርካታ መኪናዎች ተደርድረው ወይም ብዙ አስፋፊዎች ተከማችተው ሲያዩ ፍርሃት ያድርባቸዋል። የመኖሪያ አካባቢዎችን “እንደ ወረርን” የሚያስመስል ሁኔታ እንዲፈጠር አንፈልግም። የአገልግሎት ክልሉን መሸፈን የምንችልበትን መንገድ በመስክ ስምሪት ስብሰባ ላይ ማዘጋጀቱ የተሻለ ይሆናል። እንደ አንድ ቤተሰብ ያሉ ትናንሽ ቡድኖች ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ የቤቱን ባለቤቶች ሥጋት የሚቀንስ ሲሆን የአገልግሎት ክልሉንም ለመሸፈን የሚደረገውን ቅንጅት ሥራ የሚያቀል ይሆናል።

16 ሥርዓታማነት ወላጆች በአገልግሎት ክልል ውስጥ ሲሠሩ ልጆቻቸው ጥሩ ጠባይ እንዲኖራቸው መከታተልንም የሚጠይቅ ነው። ልጆች ከትላልቆች ጋር ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ የታረመ ጠባይ ማሳየት ይኖርባቸዋል። ልጆች የነዋሪዎቹን ወይም በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎችን አላስፈላጊ ትኩረት በሚስብ መንገድ እንዲጫወቱ ወይም ወዲያና ወዲህ እንዲሯሯጡ ሊፈቀድላቸው አይገባም።

17 በሻይ ረፍት ረገድም ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል። የሰኔ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ እንዲህ ብሎ ነበር:- “መስክ አገልግሎት ወጥተን ውድ የሆነውን ጊዜ በሻይ እረፍት ልናቃጥል እንችላለን። ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ትንሽ እረፍት ማድረጉ ጉልበታችንን ከማደሱም በተጨማሪ አገልግሎታችንን እንድንቀጥል ይረዳናል። ቢሆንም ብዙዎቹ ከወንድሞች ጋር አብረው በመሆን ሻይ ቡና ከማለት ይልቅ ለሰዎች በመመሥከር እንደተጠመዱ መቀጠልን መርጠዋል።”

18 ብዙዎች ሰዎችን ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ማለትም በመንገድ ላይ፣ በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እንዲሁም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው በሌሎች ቦታዎች በመሄዳቸው ግሩም ውጤቶች አግኝተዋል። በእነዚህ አካባቢዎችም ቢሆን በቃላችን ብቻ ሳይሆን በምናሳየው ምክንያታዊነትም ግሩም ምሥክርነት መስጠት እንፈልጋለን። በእያንዳንዱ ጉባኤ ውስጥ ያሉ አስፋፊዎች የአገልግሎት ክልል ወሰናቸውን ማክበር የሚኖርባቸው ሲሆን በንግድ አካባቢዎች ወይም በሥራ ቦታዎች አካባቢ የሚጓዙ እግረኞችን አሁንም አሁንም እንዳያስቆሟቸው በአንድ መንገድ ላይ፣ አደባባይ ላይ ወይም መናፈሻ ውስጥ ስንት አስፋፊዎች እንዳሉ ማስተዋል ይኖርባቸዋል። ከመንገድ ወደ መንገድ ስናገለግልም ቢሆን ፍሬያማ የመሆን ግብ በመያዝ ትኩረታችን በአገልግሎቱ ላይ እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል። ስለ ግል ጉዳያችን በማውራት መጠመድ አንፈልግም። ባብዛኛው ሲታይ ልናነጋግራቸው የምንችል ብዙ ሰዎች ስለምናገኝ ስለ ምሥራቹ ሳንናገር ብዙ ደቂቃዎች እንድናሳልፍ የሚያስገድድ ሁኔታ አይኖርም። አገልግሎታችንን ሥርዓታማና ክብር ባለው መንገድ ለማከናወን እንድንችል በጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል ሌላ ጉባኤ ለመርዳት የምንችልበት ዝግጅት እስካልተደረገልን ድረስ በጉባኤያችን የአገልግሎት ክልል ውስጥ ብቻ መሥራት ይኖርብናል።—ከ2 ቆሮንቶስ 10:13–15 ጋር አወዳድር። (የ1980 ትርጉም)

19 ለሕዝብ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ ብዙ አካባቢዎች ያሏቸው ጉባኤዎች እነዚሁኑ ቦታዎች በአገልግሎት ክልል መልክ ሸንሽነዋቸዋል። ከዚያም የአገልግሎት ክልል ካርታው ለአንድ አስፋፊ ወይም ለአንድ የአስፋፊዎች ቡድን ይሰጣል። ይህም ክልሉን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመሸፈን ከማስቻሉም በላይ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” ከሚለው የ1 ቆሮንቶስ 14:40 መሠረታዊ ሥርዓት ጋር በሚስማማ መንገድ በርካታ አስፋፊዎች በአንድ አካባቢ እንዳይሠማሩ ለማድረግ ይረዳል።

20 የሰውነት አያያዛችን ሁልጊዜ የሚያስከብርና የይሖዋን ስም ለተሸከሙ አገልጋዮች የሚገባ መሆን ይኖርበታል። የምንገለገልባቸው መሣሪያዎች ሁኔታም ከዚህ የተለየ መሆን የለበትም። ያረጁ የጽሑፍ ቦርሳዎች እንዲሁም የገጾቻቸው ጠርዞች የተጨማደዱ ወይም የቆሸሹ መጽሐፍ ቅዱሶች ሰዎቹ በመንግሥቱ መልእክት ላይ እንዳያተኩሩ ሐሳባቸውን ይሠርቁባቸዋል። አለባበስና አጋጌጥ በዙሪያችሁ ላለው ሕዝብ ማንና ምን መሆናችሁን እንዲሁም በነገሮች ሥርዓት ውስጥ ያላችሁን ቦታ የሚናገር ነው ተብሎለታል። በመሆኑም የሰውነት አያያዛችን ዝርክርክነት ወይም ግዴለሽነት የሚታይበት ወይም ደግሞ ከልክ በላይ የተብለጨለጨ እንዲሆን አንፈልግም። ይልቁንም ዘወትር ‘ለምሥራቹ የሚገባ’ መሆን ይኖርበታል።—ፊልጵ. 1:27፤ ከ1 ጢሞቴዎስ 2:9, 10 ጋር አወዳድር።

21 በ1 ቆሮንቶስ 9:26 ላይ ጳውሎስ “ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፣ ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም” ሲል ተናግሯል። የጳውሎስን ምሳሌ በመኮረጅ የእኛም ቁርጥ ውሳኔ ውጤታማና ፍሬያማ አገልግሎት ማከናወን ነው። ዛሬ ያለው የይሖዋ ‘የአንበጣ ሠራዊት’ ክፍል በመሆን በምሥክርነቱ ሥራ በቅንዓት ስለምንካፈል በክልላችን ውስጥ ላሉት ሰዎች የመዳንን መልእክት ስናደርስ ክርስቲያናዊ ምክንያታዊነትና ማስተዋል ይኑረን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ