የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/95 ገጽ 3
  • የምታንጹ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምታንጹ ሁኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስለ መንፈሳዊ ነገሮች መወያየት ያንጻል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • አዎንታዊና የምታበረታታ ሁን
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በአገልግሎት ላይ ስትሆኑ እርስ በርሳችሁ ተናነጹ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • በእምነታችን ላይ በጎነትን መጨመር የምንችለው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 7/95 ገጽ 3

የምታንጹ ሁኑ

1 ‘በሚያስጨንቅ ዘመን’ ውስጥ ስለምንኖር ሁላችንም ማበረታቻ ያስፈልገናል። (2 ጢሞ. 3:1) ጳውሎስ በእርሱ ዘመን እንኳ ይህ ነገር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በመገንዘብ ከወንድሞቹ ጋር የሚገናኝበትን ጊዜ ‘እርስ በእርሳቸው መጽናናት’ የሚችሉበት አጋጣሚ አድርጎ ለመጠቀም ጓጉቶ ነበር። ‘እርስ በርሳቸው የሚተናነጹበትን እንዲከተሉ’ ወንድሞቹን አጥብቆ አሳስቧቸዋል። (ሮሜ 1:11, 12፤ 14:19) እነዚህ ጥረቶች ‘የደቀ መዛሙርቱን ልብ ለማጽናት፣ በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ለማበረታታት’ አስችለዋል። (ሥራ 14:22) ዛሬም ይህንን የመሰለ ማበረታቻ በጣም ያስፈልገናል።

2 በምንናገረው ነገር ሌሎችን የምናንጽ መሆን እንችላለን። ከአፋችን የሚወጡትን ቃላት በተገቢው መንገድ ስንጠቀምባቸው “በብር ፃሕል ላይ እንደተቀመጠ የወርቅ ፖም” ሊሆኑ ይችላሉ። (ምሳሌ 25:11 አዓት) በስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ ‘እርስ በርሳችን እንበረታታለን።’ (ዕብ. 10:25 የ1980 ትርጉም ) ተሞክሮዎችን ስንናገር፣ ምስጋና ስናቀርብ ወይም መንፈሳዊ ነገሮችን ስንወያይ ምላሳችንን በሚያንጽ መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን። እንዲህ ያለው ገንቢ የምላስ አጠቃቀም “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም” ነው።— ኤፌ. 4:29

3 የሚያንጹ ነገሮችን ተናገር፦ በፊልጵስዩስ 4:8 ላይ ጳውሎስ የምንናገራቸውን ነገሮች በተመለከተ ልንከተለው የሚገባ ጠቃሚ ምክር ሰጥቶናል። እውነተኛ የሆነውን ነገር [“ቁም ነገር” አዓት ]፣ ጽድቅ፣ ንጹሕ፣ ፍቅር፣ መልካም ወሬ፣ በጎነትና ምስጋና ያለበትን ነገር ማሰብ እንዳለብን ተናግሯል። የምንናገረው ነገር በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ከሆነ እውነተኛና ለሌሎች ጠቃሚ እንደሚሆን ምንጊዜም እርግጠኞች መሆን እንችላለን። (ዮሐ. 17:17) ራሳችንን ለይሖዋ በመወሰን የወሰድነው ክርስቲያናዊ እርምጃ፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የተማርናቸው ነገሮች፣ አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ የምናከናውንበት መንገድና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ነገሮች በቁም ነገር የምንመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው። በአምላክ ቃል ውስጥ ስላሉት መስፈርቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች የምናደርገው ገንቢ ጭውውት “መዳን የሚገኝበትን ጥበብ” እንደሚያስገኝልን ጥርጥር የለውም። (2 ጢሞ. 3:15) ንጹሕ በሆነው የይሖዋ ድርጅት ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ላላቸው ንጹሕ ሥነ ምግባር ያለንን አድናቆት ልንገልጽ እንችላለን። ወንድሞቻችን በፍቅራዊ ደግነት ያደረጉትን ነገር ልናሞግስ እንችላለን። (ዮሐ. 13:34, 35) መልካም ወሬ ያለባቸው ነገሮች በወንድሞቻችን መካከል ስለምንመለከታቸው ገንቢ ክርስቲያናዊ ባሕርያት ስለሆኑት ስለ እምነት፣ ደስታ፣ ሰላምና ትዕግሥት መናገርን ይጨምራል። እንደ በጎነትና ምስጋና ስለመሳሰሉ ነገሮች አንስቶ መጫወቱ ሌሎችን ‘ለማነጽ የሚጠቅም’ ነው።— ሮሜ 15:2

4 ተስፋ አስቆራጭ የሆኑት የዚህ ዓለም አስጨናቂ ሁኔታዎች በየዕለቱ ያጋጥሙናል። እነዚህን ነገሮች ወደጎን ገሸሽ አድርገን ከወንድሞቻችን ጋር ፍቅራዊ ግንኙነት ማድረጉ ምንኛ የሚያድስ ነው! ከወንድሞቻችን ጋር የምናሳልፈው ውድ ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው። ሁልጊዜ የምናበረታታና የምናንጽ ከሆንን ‘መንፈሴን አሳርፈዋል’ ብለው ሌሎች ስለ እኛ ከልባቸው መናገር ይችላሉ።።— 1 ቆሮ. 16:18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ