የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/96 ገጽ 8
  • እውነትን መናገራችሁን ቀጥሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነትን መናገራችሁን ቀጥሉ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • “እምነት ከመስማት ነው”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ከእውነተኛው አምላክ የሚገኘው እውቀት ወደ ሕይወት ይመራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ከአምላክ የሚገኘው እውቀት ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 5/96 ገጽ 8

እውነትን መናገራችሁን ቀጥሉ

1 ሐዋርያት “እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” ብለው ነበር። (ሥራ 4:20) ዛሬም ቢሆን እኛም እውነትን ከመናገር ወደ ኋላ ማለት የለብንም። ምንም እንኳ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ማሰራጨት ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት የሚያስችል ቢሆንም ፍላጎት ላላቸው ሰዎች እውነትን ይበልጥ ለማስተማር ተመልሰን መሄድ አለብን።

2 “ጦርነት የማይኖርበት ጊዜ” የሚል ርዕስ ያለውን የሚያዝያ— ሰኔ ልዩ እትም “ንቁ!” ላበረከትክለት ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ እንዲህ ብለህ በመጠየቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ትችላለህ:-

◼ “ባለፈው ጊዜ ብሔራት ስለሚያደርጓቸው ጦርነቶችና ሃይማኖት በእነዚህ ጦርነቶች ውስጥ ስለሚጫወተው ሚና ተነጋግረን ነበር። እነዚህ ሁኔታዎች መጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ ቀን ብሎ በሚጠራው ጊዜ እንደምንኖር የማያሻማ ማረጋገጫ የሚሰጡ እንደሆኑ ያውቁ ነበርን? [ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አሳየው። በምዕራፍ 18 ውስጥ የሚገኘውን አንቀጽ 4 አንብብለትና በገጽ 150-153 የሚገኙትን ሥዕሎች ጎላ አድርገህ ግለጽ።] ይህ መጽሐፍ ይህንንና በዚህ ርዕስ ማውጫ ላይ የተዘረዘሩ ሌሎች 29 ርዕሶችን ያብራራል። [ገጽ 5⁠ን አሳየው።] ይህ መጽሐፍ እነዚህን አስፈላጊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ለማስተዋል የሚረዳዎ እንዴት እንደሆነ ባሳይዎ ደስ ይለኛል።” ፈቃደኛ ከሆነ ከገጽ 7 ጀምራችሁ ማጥናት ጀምሩ።

3 ሌላ ጊዜ ተመልሰህ አሁንም እንኳ ደህንነት የሰፈነበት ሕይወት መምራት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ እንደምትነግራቸው ቃል ገብተህ ከነበረ እንዲህ ማለት ትችላለህ:-

◼ “ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘን ዕለት ስለ ሰው የወደፊት ዕጣ ብሩህ አመለካከት እንዲኖርን የሚያበረታታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አሳይቼዎት ነበር። ዛሬ ደግሞ በአሁኑ ጊዜም እንኳ ደህንነት ሊሰጠን የሚችለው ማን ስለመሆኑ የሚናገር ጥቅስ ባሳይዎ ደስ ይለኛል።” መዝሙር 4:8⁠ን አንብብ። እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 168 አውጣና አንቀጽ 19⁠ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ:- “እንዲህ ያለ ደህንነት የሰፈነበት ሕይወት መምራት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ያለ ክፍያ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቢደረግልዎ አይደሰቱም?” ፈቃደኝነቱን ከገለጸ ወደ ምዕራፍ 1 ሂድ።

4 በተመላልሶ መጠየቁ ወቅት እንደሚከተለው በማለት ጥናት ለማስጀመር ቀጥተኛ ግብዣ ማቅረብ ትችላለህ:-

◼ “በማንኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ትምህርቶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት መጽሔቶቻችንን በመላው ዓለም እናሰራጫለን። ሰዎች ላወቁት ነገር አድናቆት ካደረባቸው ያለ ክፍያ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲያደርጉ እንጋብዛቸዋለን። [በመጠበቂያ ግንብ የጀርባ ሽፋን ላይ የሚገኘውን ‘መጥተን እንድናነጋግርዎ ይፈልጋሉን?’ የሚለውን ሣጥን አሳየው።] ለማስጠናት የምንጠቀመው በዚህ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት (ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ) በሚባለው መጽሐፍ ነው። ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ በአጭሩ ላሳይዎ።”

5 እውነትን መናገራችንን ከቀጠልን ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑና ጥሩ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች እንደምናገኝ እርግጠኛ መሆን እንችላለን።— ማር. 4:20

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ