የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/97 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከስብሰባ አዳራሹ ቤተ መጻሕፍት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
  • ቲኦክራሲያዊ ቤተ መጻሕፍት ማደራጀት የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ከማስቀመጥ ይልቅ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የመንግሥት አዳራሽ ቤተ መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረገ አዲስ ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 4/97 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን

◼ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ምን ምን ጽሑፎች ሊኖሩ ይገባል?

የአምላክ ሕዝቦችን ለመጥቀም ሲባል ብዛት ያላቸው መንፈሳዊ ጽሑፎች ተዘጋጅተዋል። ብዙ አስፋፊዎች ሁሉም ጽሑፎች ስለሌሏቸው በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ የሚገኘው ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት ምርምር ለማድረግ የሚረዱ በሌላ ቦታ የማይገኙ ጽሑፎችን ለማግኘት ያስችላል። ስለዚህም ቤተ መጻሕፍቱ የተለያየ ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ ማኅበሩ በቅርቡ ያወጣቸውን አዳዲስ ጽሑፎች፣ የመንግሥት አገልግሎታችን ቅጂዎችን፣ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ጥራዞችንና የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ኢንዴክስ ን የያዘ መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም አንድ ጥሩ ዘመናዊ መዝገበ ቃላት መኖር አለበት። በቀላሉ የሚገኝ ከሆነም ኢንሳይክሎፔድያዎች፣ አትላሶች፣ የሰዋስውና የታሪክ ማመሳከሪያ መጻሕፍት ቢኖሩ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በይበልጥ የሚያሳስበን “ታማኝና ልባም ባሪያ” ያዘጋጃቸውን ጽሑፎች ማግኘት መሆን ይኖርበታል።​— ማቴ. 24:​45

በአንዳንድ ወቅቶች አጠያያቂ መጻሕፍት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ተቀምጠው እንደተገኙ ሪፖርት ተደርጓል። ልብ ወለድ ጽሑፎችን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተሰነዘሩ ትችቶችን ወይም ፍልስፍናን እንዲሁም መናፍስታዊ እምነትን የሚያራምዱ መጽሐፎችን በቤተ መጻሕፍቱ ውስጥ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም። ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት ሊያቅፋቸው የሚገባው ተጠቃሚ የሆኑት ሰዎች የማያቋርጥ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ የሚያግዙ ጽሑፎችን ብቻ ነው።​— 1 ጢ⁠ሞ. 4:​15

ምንም እንኳ ክትትል ለማድረግ እንዲረዳው ሌላ ወንድም መመደብ ቢችልም የቤተ መጻሕፍቱ ኃላፊ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ነው። እርሱም አዳዲስ ጽሑፎች እንደወጡ በማምጣት በቤተ መጻሕፍቱ ወቅታዊ የሆኑ ጽሑፎች መኖራቸውን መከታተል ይኖርበታል። እያንዳንዱ መጽሐፍ በሽፋኑ ውስጠኛ ክፍል ግልጽ በሆነ መንገድ የባለ ንብረቱ ጉባኤ ስም መጻፍ ይኖርበታል። መጠገን ወይም መተካት የሚያስፈልጋቸው መጻሕፍት እንዳሉ ለማረጋገጥ በየዓመቱ መጽሐፎቹ መመርመር ይኖርባቸዋል።

ቤተ መጻሕፍቱን ጥሩ አድርጎ በመያዝ በኩል እያንዳንዱ ግለሰብ ትብብር ሊያደርግ ይችላል። መጻሕፍቱ በሚያዙበትና በሚነበቡበት ጊዜ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ሕፃናት እንዲጫወቱባቸው መፍቀድ አይገባም፤ ወይም ማንኛውም ሰው በመጽሐፎቹ ላይ ማስመር የለበትም። ለማሳሰብ ያህል መጽሐፎችን ከመንግሥት አዳራሹ ውጪ ይዞ መውጣት ክልክል መሆኑን የሚገልጽ ጽሑፍ ሊታይ በሚችል ቦታ ላይ መለጠፍ ይቻላል።

በየጊዜው አዳዲስ ጉባኤዎች ስለሚመሠረቱ ብዙ ቤተ መጻሕፍት የሚኖራቸው መጽሐፍ መጠን አነስተኛ መሆኑ የማይቀር ነው። የቆዩ ጽሑፎቻችን ያሏቸው አንዳንድ አስፋፊዎች ለጉባኤው በልግስና ለመስጠት ሊያስቡ ይችላሉ። ሽማግሌዎች ማኅበሩ እንደገና የሚያትማቸውን የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች ለማዘዝ ይፈልጉ ይሆናል። በዚህ መንገድ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት በአምላክ ቃል ውስጥ ያሉትን የተደበቁ ውድ ሃብቶች በመግለጥ ሌሎች እውቀት፣ ጥበብና ማስተዋል እንዲያገኙ በመርዳት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።​— ምሳሌ 2:​4-6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ