ከማስቀመጥ ይልቅ ተጠቀሙባቸው
ብዙ ጉባኤዎች የቆዩ ጽሑፎች ክምችት አላቸው። ታዲያ ለቲኦክራሲያዊ ቤተ መጻሕፍትህ የሚሆኑ ጽሑፎችን ለምን አትወስድም? እነዚህን ጽሑፎች ዎችታወር ላይብረሪ ላይ ልታገኛቸው እንደምትችል እሙን ነው። ይሁን እንጂ የታተሙት ጽሐፎች ያሉህ መሆኑ ይጠቅምሃል። ጥሩ እድገት እያደረገ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አለህ? ከሆነ የቆዩ ጽሑፎችን በመውሰድ የራሱን የግል ቤተ መጻሕፍት እንዲያደራጅ አበረታታው። የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካቹ በጉባኤው ውስጥ ያሉት የቆዩ ጽሑፎች በሙሉ በመንግሥት አዳራሹ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ መኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት። እነዚህ ጽሑፎች አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ዋጋ አላቸው። የጉባኤውን የጽሑፍ መደርደሪያ ከሚያጨናንቁ ይልቅ ወስደን ብንጠቀምባቸው የተሻለ ነው!