የጥያቄ ሣጥን
◼ ከጉባኤ የአገልግሎት ኮሚቴ አባል ከአንዱ በምናገኘው መመሪያ አገልግሎት ላቆመ ወንድም ወይም ላቆመች እህት ዛሬም የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራቱ ተገቢ ይሆናልን?
ሽማግሌዎች አገልግሎት ያቆሙትን የጉባኤ አባላት ጨምሮ ጉባኤውን በእረኝነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። እንደነዚህ ላሉት ሰዎች ጉብኝት በማድረግ ምን ዓይነት እርዳታ በግል ቢሰጣቸው ጥሩ እንደሆነ ይወስናሉ። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም አገልግሎት ያቆመው ግለሰብ በግል በሚደረግለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አማካኝነት እንዲጠቀም ማድረግን ሊጨምር ይችላል። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተባለው መጽሐፍ በገጽ 103 ላይ ከዚህ ዝግጅት እነማን መጠቀም እንደሚችሉ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ እንደሚወስን ይገልጻል።
እገዛውን በተሻለ መንገድ ማን ሊሰጥ እንደሚችል፣ የትኛው ርዕሰ ጉዳይ መጠናት እንዳለበትና የትኛው ጽሑፍ ይበልጥ ጠቃሚ እንደሚሆን የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ይወስናል። ግለሰቡን መጀመሪያ ያስጠናው ወይም ቀደም ሲል የሚያውቀውና የሚያከብረው ሰው ቢሆንለት በተሻለ መንገድ ሊረዳው ይችላል። ጥሩ ችሎታ ያላትና የጎለመሰች አንዲት እህት አገልግሎት ያቆመችን እህት እንድትረዳ ልትጠየቅ ትችላለች። ብዙውን ጊዜ ሌላ አስፋፊ ከተመደበው አስጠኚ ጋር አብሮ መሄዱ አስፈላጊ አይደለም። የተመደበው አስፋፊ ጥናት በሚመራበት ጊዜ ሰዓት፣ ተመላልሶ መጠየቅና ጥናት ሪፖርት ሊያደርግ ይችላል።—የኅዳር 1987 የመንግሥት አገልግሎታችን (እንግሊዝኛ) ገጽ 1–2ን ተመልከቱ።
ሰውየው የተጠመቀ እንደመሆኑ መጠን በጥቅሉ ሲታይ ጥናቱ ለረዥም ጊዜ መቀጠል አይኖርበትም። ዋናው ግብ አገልግሎት ያቆመው ግለሰብ በሁሉም የጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት እንዲጀምርና የምሥራቹ አዘውታሪ አስፋፊ እንዲሆን መርዳት ነው። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ እንዲህ ዓይነቶቹ ጥናቶች የሚያደርጉትን እድገት መከታተል ይኖርበታል። ይህ ፍቅራዊ እገዛ እነዚህ ወንድሞችና እህቶች በይሖዋ ፊት የራሳቸውን የኃላፊነት ሸክም መሸከም እንዲችሉና በእውነት ‘ሥር ሰደውና ተመሥርተው’ መቆም እንዲችሉ መርዳት ይኖርበታል።—ኤፌ. 3:17፤ ገላ. 6:5