የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/99 ገጽ 8
  • ሙስሊም ቢያጋጥማችሁ ምን ትላላችሁ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሙስሊም ቢያጋጥማችሁ ምን ትላላችሁ?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እነዚህን ብሮሹሮች እየተጠቀማችሁባቸው ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • “አዎንታዊ አመለካከት በመያዝ ምሥራቹን ማቅረብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ለሌሎች ልባዊ ኣሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 11/99 ገጽ 8

ሙስሊም ቢያጋጥማችሁ ምን ትላላችሁ?

1 ሙስሊም ለሆነ ሰው የመመሥከር አጋጣሚ አግኝተህ ታውቃለህ? ከሆነ፣ ሙስሊሞች በአምላክ ላይ ጽኑ እምነት እንዳላቸው ሳትገነዘብ አትቀርም። ይሁን እንጂ የይሖዋ ነቢያት ወደፊት ምድር ገነት እንደምትሆን ስለተነበዩት ነገር ምንም አያውቁም። እኛ ደግሞ ይህን ተስፋ ልናካፍላቸው እንፈልጋለን። (1 ጢሞ. 2:3, 4) ቀጥሎ የቀረበው ሐሳብ ጥሩ ምሥክርነት እንድትሰጥ ሊረዳህ ይገባል።

2 ሙስሊሞች በአላህ ማለትም በአምላክ የሚያምኑ ሲሆን መሐመድ ደግሞ የአምላክ ነቢይ እንደሆነ ያምናሉ። ቅዱስ መጽሐፋቸው ቁርአን ይባላል። ሃይማኖታቸው “መገዛት” የሚል ትርጉም ባለው እስልምና በሚል ስያሜ ይታወቃል። ቁርአን መዋሸትና የጣዖት አምልኮ ስህተት እንደሆነ፣ አምላክ የሥላሴ ክፍል ሳይሆን አንድ ብቻ መሆኑን ይገልጻል። በተጨማሪም ነፍስ እንደማትሞት፣ እሳታማ ሲኦል እንዳለና ገነት በሰማይ እንደሚገኝ ያስተምራል። ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነ ቢቀበሉም ለውጥ ተደርጎበታል የሚል እምነት አላቸው። በአንጻሩ ደግሞ ቁርአን እስከ አሁን ድረስ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ምንም ሳይበረዝ ተጠብቆ መቆየቱን ያምናሉ።

3 ወዳጃዊ መንፈስ ያላችሁ፣ ዘዴኞችና አስተዋዮች ሁኑ፦ ከአንድ ሙስሊም ጋር ስትወያዩ ወዳጃዊና ዘዴኞች ሁኑ። (ምሳሌ 25:15) ሙስሊሞች የሚያምኑባቸውን ነገሮች በጥብቅ እንደሚከተሉና አብዛኞቹንም ነገሮች የተማሩት በቃል እንደሆነ አትዘንጉ። በመሆኑም ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ማስረዳትና የአምላክ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ መመርመር የመንፈሳዊ ሕይወታቸው ክፍል ሆኖ አያውቅም። (ሮሜ 12:2) ሙስሊሞችን ለመርዳት ትዕግሥተኛ መሆንና አመለካከታቸውን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው።—1 ቆሮ. 9:19-23

4 በሙስሊሙ ሰው አስተሳሰብ የሕዝበ ክርስትና ክፍል እንደሆንክ የሚያስመስሉ አባባሎችን ከመጠቀም ተቆጠብ። የኦርቶዶክስም ሆነ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ክፍል አለመሆንህን ግልጽ አድርግለት። መጽሐፍ ቅዱስን ፈጣሪ የሰጠን መጽሐፍ እያልክ ተናገር። ሙስሊሞች “የአምላክ ልጅ” የሚለው አባባል ስለማያስደስታቸው በአብዛኛው በዚህ አጠራር አለመጠቀሙ ወይም ሰውየው መንፈሳዊ እድገት እስኪያደርግ ድረስ ይህን ርዕስ አለመወያየቱ ጥሩ ይሆናል። ሆኖም ኢየሱስ ነቢይ ወይም መልእክተኛ እንደሆነ በመጥቀስ ስለ እርሱ መናገር ትችላለህ። አትከራከር። ሰውየው መቆጣት ከጀመረ ትሕትና በተሞላበት መንገድ ወዲያውኑ ተለይተኸው ሂድ።

5 ሰብሰብ ካሉ ሰዎች ጋር ከመነጋገር ይልቅ በተናጠል ከአንድ ሰው ጋር መነጋገሩ የተሻለ ነው። በአብዛኛው ሴቶች ሴቶችን፣ ወንዶች ደግሞ ወንዶችን ቢያነጋግሩ ይመረጣል። አንዳንድ ጊዜ ለየት ያለ ሁኔታ እንደሚኖር የታወቀ ቢሆንም ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ መጠቀም ግን ያስፈልጋል። በተጨማሪም ብዙ ሙስሊሞች የሴቶችን አለባበስና አበጣጠር በተመለከተ በእነርሱ አመለካከት ተገቢ እንዳልሆነ በሚያስቡት ነገር በቀላሉ ይጎዳሉ። እህቶች ለዚህ ጉዳይ ትኩረት መስጠት አለባቸው።—1 ቆሮ. 10:31-33

6 የመነጋገሪያ ርዕስ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች፦ ስለ አምላክ ታላቅነትና ስለ አፍቃሪነቱ ያለህን ስሜት በግልጽ ተናገር። አምላክ አንድ መሆኑን (ሥላሴ አለመሆኑን) እና የጣዖት አምልኮ ስህተት መሆኑን ከልብ የምታምን ሰው መሆንህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል። በብዙ ሃይማኖታዊ ሰዎች ዘንድ በግልጽ ስለሚታየው ዛሬ በዓለም ላይ ስላለው ክፋት ማለትም ስለ ጦርነት፣ የሕዝብ ዓመፅ፣ የዘር ጥላቻና ግብዝነት ተናገር።

7 የአምላክ መመሪያ—ወደ ገነት የሚያደርሰን መንገድ (እንግሊዝኛ) የተባለው ብሮሹር ከሙስሊሞች ጋር ውይይት ለመጀመር ልንጠቀምባቸው የምንችልባቸውን ርዕሶች በተመለከተ ተጨማሪ እውቀት ይሰጠናል። ይህ በሚኖሩበት አካባቢ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት የግል ምርጫቸው እንደሆነ የሚሰማቸው ሙስሊሞችን ሊማርክ በሚችል ሁኔታ የተዘጋጀ ብሮሹር ነው።

8 ቀጥሎ ያለውን አቀራረብ በመጠቀም እንዲህ ማለት ትችላለህ:-

◼ “ሙስሊሞችን ለማነጋገር ለየት ያለ ጥረት እያደረግሁ ነው። ስለ ሃይማኖታችሁ የሚናገሩ ጽሑፎችን አንብቤ ነበር። ሙስሊሞች በአንድ እውነተኛ አምላክና በሁሉም ነቢያት ያምናሉ ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ምድር ወደ ገነትነት እንደምትለወጥ ስለሚናገር አንድ የቆየ ትንቢት ብነግርዎ ደስ ይለኛል። ነቢዩ ምን ብሎ እንደጻፈ ላንብብልዎ? [ኢሳይያስ 11:6-9⁠ን አንብብ።] ይህ ትንቢት በዚህ ብሮሹር ውስጥ የሚገኝ ከቁርአን የተወሰደ አንድ ጥቅስ እንዳስታውስ ያደርገኛል።” የአምላክ መመሪያ የተባለውን ብሮሹር ገጽ 9 ላይ ገልጠህ ጻድቃን ምድርን እንደሚወርሱ የሚናገረውን ጎላ ብሎ የተጻፈውን ጥቅስ አንብብ። ሰውየው ፍላጎት ካሳየ ቀጥሎ ባለው ገጽ ላይ ከአንቀጽ 7 እስከ 9 ያሉትን ሐሳቦች በማብራራት ውይይቱን ቀጥል። ብሮሹሩን ስጠውና ተመልሰህ የምትመጣበትን ቀጠሮ ያዝ።

9 ለአንድ ሙስሊም የአምላክ መመሪያ የተባለውን ብሮሹር እንዲመረምር ሐሳብ ስታቀርብለት ነገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደሆነ ከመንገር ይልቅ ውይይት እንደሆነ ብትነግረው የተሻለ ይሆናል። ብሮሹሩን ካስጨረስከው በኋላ ተማሪው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማጥናት የሚችልበት ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ግልጽ ነው። በተለይ ለሙስሊሞች ተብለው ከተዘጋጁት ሌሎች ጽሑፎች መካከል ሃው ቱ ፋይንድ ዘ ሮድ ቱ ፓረዳይዝ የተባለው ትራክትና ዘ ታይም ፎር ትሩ ሰብሚሽን ቱ ጎድ የተባለው ቡክሌት ይገኙበታል።

10 ከላይ የተጠቀሱትን ሙስሊሞች የሚያምኑባቸውንና በቀላሉ የሚጎዱባቸውን ነጥቦች በአእምሯችን ከያዝን ለሙስሊሞች የምናበረክተውን ጽሑፍ ስንመርጥም ሆነ ለእነርሱ የምንመሠክርበትን መንገድ በተመለከተ አስተዋዮች መሆን እንችላለን። ሁሉም ዓይነት ሰዎች የይሖዋን ስም ጠርተው እንዲድኑ ለመርዳት የምናደርገውን ጥረት ይሖዋ መባረኩን እንዲቀጥል ምኞታችን ነው።—ሥራ 2:21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ