መጽሐፍ ቅዱስ—የሰው ልጅ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ ለተባለው የቪዲዮ ክር አድናቆት ማሳየት
የሚከተሉት ጥያቄዎች ይህንን የቪዲዮ ክር ስትመለከት ያስተዋልካቸውን ነጥቦች ጎላ አድርገው የሚገልጹ ናቸው:- (1) መጽሐፍ ቅዱስ ተወዳዳሪ የሌለው መጽሐፍ መሆኑን የሚያሳዩት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? (2) መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ጥንታዊ መጽሐፍ ሆኖ ሳለ ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር እንደሚስማማ የሚጠቁም አንድ ምሳሌ ጥቀስ። (3) ዛሬ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በእጅ ከተጻፉት ቅጂዎች ልዩነት እንደሌለው እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (4) በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በአጻጻፍ ረገድ ልዩ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? ይህስ ስለምን ነገር እርግጠኛ እንድትሆን ይረዳሃል? (5) ጆን ዊክሊፍ፣ ጆሃነስ ጉተምበርግ፣ ዊልያም ቲንደል፣ ሜሪ ዮንስና ቻርልስ ቴዝ ራስል የአምላክ ቃል በዓለም ዙሪያ እንዲሰራጭ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያበረከቱት እንዴት ነው? (6) ቤተ ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የከረረ ተቃውሞ ያስነሳችው እንዴት ነው? ሆኖም ሳይጠፋ እስከ ዘመናችን እንዲቆይ ያስቻለው ምንድን ነው? (7) የይሖዋ ድርጅት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲተረጎምና እንዲታተም በማድረግ በኩል ምን ነገር አከናውኗል? (8) መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ተግባራዊ ምክር የቁማር ሱስ ያለባቸውን (1 ጢሞ. 6:9, 10)፣ ከትዳር ጓደኛቸው የተለያዩትንና ክህደት የተፈጸመባቸውን (1 ቆሮ. 13:4, 5፤ ኤፌ. 5:28-33) እንዲሁም ቁሳዊ ሃብት በማሳደድ የተጠመዱትን ሰዎች (ማቴ. 16:26) የረዳው እንዴት ነው? (9) የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ በዓለም የሚታየውን የብሔር፣ የጎሣና የዘር ጥላቻ ለማሸነፍ እንደሚረዳ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ? (10) መጽሐፍ ቅዱስ ያዘለውን መልእክት መማርህ ከፍተኛ ደስታ ያስገኘልህ በምን መንገዶች ነው? (11) ይህንን ቪዲዮ እነማን ቢያዩት የሚጠቀሙ ይመስልሃል? እንዲያዩ ልትረዳቸው የምትችለውስ እንዴት ነው?