መጽሐፍ ቅዱስ—የእውነትና የትንቢት መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስ—የእውነትና የትንቢት መጽሐፍ የተባለው ዲቪዲ ከያዛቸው ሦስት ፊልሞች የመጀመሪያው፣ የሰው ልጅ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ የሚለው ነው። ይህን ፊልም ከተመለከታችሁ በኋላ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
(1) መጽሐፍ ቅዱስ ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር የሚስማማው በየትኞቹ መንገዶች ነው? (2) በዛሬው ጊዜ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በእጅ ከተጻፉት ቅጂዎች ጋር አንድ ዓይነት ለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን? (3) በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በአጻጻፍ ረገድ ልዩ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? (4) ጆን ዊክሊፍ፣ ጆሃነስ ጉተምበርግ፣ ዊልያም ቲንደል፣ ጆን ሁስ፣ ማርቲን ሉተር፣ ካሲዮዶሮ ዴ ሬና እና ቻርልስ ቴዝ ራስል የአምላክ ቃል በዓለም ዙሪያ እንዲሰራጭ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያበረከቱት እንዴት ነው? ቤተ ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የከረረ ተቃውሞ ያስነሳችውስ እንዴት ነው? (5) መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ጠቃሚ ምክር የጤና እክል ያለባቸውን (መዝ. 34:8)፣ የቁማር ሱስ ያለባቸውን (1 ጢሞ. 6:9, 10)፣ ከትዳር ጓደኛቸው የተለያዩትንና ክህደት የተፈጸመባቸውን (1 ቆሮ. 13:4, 5፤ ኤፌ. 5:28-33) እንዲሁም ቁሳዊ ሃብት በማሳደድ የተጠመዱ ሰዎችን (ማቴ. 16:26) የረዳው እንዴት ነው? (6) የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ በዓለም የሚታየውን የብሔር፣ የጎሣና የዘር ጥላቻ ለማሸነፍ እንደሚረዳ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ? (ሉቃስ 10:27) (7) የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በጥብቅ ለመከተል መጣርህ ከፍተኛ ደስታ ያስገኘልህ በየትኞቹ መንገዶች ነው? (8) ይህን ቪዲዮ በመጠቀም ሌሎችን መርዳት የምትችለው እንዴት ነው?—የየካቲት 2006 የመንግሥት አገልግሎታችንን ገጽ 8 ተመልከት።