የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/01 ገጽ 3
  • በአገልግሎታችሁ ‘ትጉ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአገልግሎታችሁ ‘ትጉ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በምሥራቹ ሥራ በከፍተኛ ትጋት መሳተፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ሚያዝያ—‘ጠንክረን የምንሠራበትና የምንጋደልበት’ ወር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • በሚያዝያ 2000 ከምንጊዜውም የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 4/01 ገጽ 3

በአገልግሎታችሁ ‘ትጉ’

1 ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሳለ በድንኳን ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንደነበር ስናነብ ሥራው የመስበክ አጋጣሚውን ገድቦበታል ብለን እናስብ ይሆናል። ይሁን እንጂ ሥራ 18:​5 እንደሚናገረው “ጳውሎስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።” (በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) ጳውሎስ በስብከቱ ሥራ ያን ያህል የተጋው ለምን ነበር? በቆሮንቶስ ብዙዎች አማኝ ሆነው የነበረ ቢሆንም በዚያች ከተማ ገና ደቀ መዛሙርት የሚሆኑ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ጌታ አረጋግጦለት ነበር። (ሥራ 18:​8-11) እኛስ በአገልግሎታችን እንድንተጋ የሚያደርግ ተመሳሳይ ምክንያት ይኖረን ይሆን? አዎን። ብዙ ሰዎች ሊገኙና እውነትን ሊማሩ ይችላሉ።

2 በሚያዝያ ተጨማሪ ሰዓታት በአገልግሎት አሳልፉ:- በየወሩ ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ መጠመድ እንደምትፈልጉ የታወቀ ነው። ሆኖም አንዳንድ ወራት በዚህ ሥራ ‘እንድንተጋ’ ሰፊ አጋጣሚ ይከፍቱልናል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት የሚያዝያ ወር ነው። በዚህ ወር ረዳት አቅኚ ለመሆን ወይም አገልግሎትህን ከፍ ለማድረግ ሁኔታዎችህ ፈቅደውልሃልን? ይህን እያደረጉ ያሉ ብዙ አስፋፊዎች በእጅጉ ተባርከዋል። (2 ቆ⁠ሮ. 9:​6) አቅምህ የሚፈቅድልህን ያህል ካደረግህ ይሖዋ የሚደሰተው በምታቀርበው የሙሉ ነፍስ አገልግሎት እንደሆነ አስታውስ። (ሉቃስ 21:​2-4) ያለህበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በሚያዝያ በአገልግሎት ‘ለመትጋት’ ግብ አውጣ። እንዲሁም ያደረግኸው ጥረት ከቀረው የይሖዋ ሕዝብ ሪፖርት ጋር እንዲደመርልህ በወሩ መጨረሻ ላይ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት መመለስህን አትርሳ።

3 በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ አዳዲስ ሰዎችን ጎብኟቸው:- ባለፈው ዓመት በአገራችን 16, 201 ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኝተው ነበር። የዚህ ዓመት የተሰብሳቢ ቁጥር ደግሞ ወደፊት የምናየው ይሆናል። ያም ሆኖ የሚደርሱት ሪፖርቶች ታላቅ “መከር” እንደሚጠብቀን የሚጠቁሙ ናቸው። (ማቴ. 9:​37, 38) ስለሆነም በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን በመንፈሳዊ ለመርዳት በተቻለ መጠን ቶሎ ተመልሳችሁ ለመጎብኘት ዝግጅት አድርጉ። ሄደን ለመጎብኘት ዛሬ ነገ የምንል ከሆነ ‘ክፉው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን የመንግሥት ቃል እንዲነጥቅ’ በር እንከፍትለታለን። (ማቴ. 13:​19) ቶሎ መጎብኘታችሁ በአገልግሎታችሁ ‘እንደምትተጉ’ የሚያሳይ ይሆናል።

4 አገልግሎት ያቆሙትን መርዳታችሁን ቀጥሉ:- በየካቲት ወር አገልግሎት ያቆሙትን ለመርዳት ልዩ ጥረት ተጀምሯል። እስከ አሁን የእረኝነት ጉብኝት ያልተደረገላቸው አገልግሎት ያቆሙ ሰዎች ካሉ ሽማግሌዎች ሚያዝያ ከመገባደዱ በፊት ሄደው ለመጎብኘት ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ሽማግሌዎች ግለሰቡን ለዚህ ያበቃው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅና ይሖዋን ማገልገሉን እንዲቀጥል እንዴት እንደሚረዳ ለመወሰን ጥረት ያደርጋሉ። እንደዚህ ያለው ፍቅራዊ እርዳታ ሽማግሌዎች “የእግዚአብሔርን መንጋ” እንዲጠብቁ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቁም ነገር እንደሚመለከቱት ያሳያል። (1 ጴ⁠ጥ. 5:​2፤ ሥራ 20:​28) የመስከረም 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-3 ሽማግሌዎች አገልግሎት ያቆሙ ሰዎች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉትን አምስት ዓይነተኛ ችግሮች ለመፍታት በሚሞክሩበት ጊዜ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን ግሩም ሐሳቦች ይዟል። አንዳንዶች በሚያዝያ በመስክ አገልግሎት በመካፈል እንደገና ይነቃቃሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

5 ሌሎች ያልተጠመቁ አስፋፊ እንዲሆኑ እርዱ:- ልጆቻችሁ የምሥራቹ አዲስ አስፋፊ ለመሆን አስፈላጊውን ብቃት አሟልተዋልን? መጽሐፍ ቅዱስን የምታስጠኗቸው ሌሎች ሰዎችስ? አስፋፊ ለመሆን የሽማግሌዎችን ፈቃድ የሚያገኙ ከሆነ አገልግሎት ለመጀመር ሚያዝያ ግሩም አጋጣሚ አይሆንላቸውምን? አንድ ሰው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹርና እውቀት መጽሐፍን አጥንቶ ከጨረሰና እድገት እያደረገ ከሆነ በሁለተኛ መጽሐፍ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን መቀጠል ይቻል ይሆናል። (ሁለተኛው መጽሐፍ የአምልኮ አንድነት ቢሆን ይመረጣል።) ግብህ ተማሪው እውነትን በጥልቅ እንዲያስተውል፣ ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን እንዲበቃ እንዲሁም ራሱን የወሰነና የተጠመቀ የይሖዋ ምሥክር እንዲሆን መርዳት ነው።​—⁠ኤፌ. 3:​17-19፤ 1 ጢ⁠ሞ. 1:​12፤ 1 ጴ⁠ጥ. 3:​21

6 ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችህ የማያቋርጥና ልባዊ አሳቢነት ማሳየትህ ውሎ አድሮ እውነትን የራሳቸው እንዲያደርጉ ሊረዳቸው ይችላል። አንድ የይሖዋ ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግላቸው ልባዊ ፍላጎት ያላቸው አረጋዊ ባልና ሚስት አገኘ። ሆኖም ባልና ሚስቱ ጥናት ለመጀመር የያዙትን ቀጠሮ ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት አፈረሱ። ከዚያ በኋላ ጥናቱ ተጀመረ። ከዚያም ባልና ሚስቱ ቀጠሮውን በየሁለት ሳምንቱ ለማለት ይቻላል ያፈርሱ ነበር። በመጨረሻ ግን ሚስትየው እድገት አድርገው ተጠመቁ። ያስጠናቸው ወንድም “ሚስትየው ከተጠመቁ በኋላ የደስታ እንባ በዓይናቸው ግጥም ሲል እኔና ባለቤቴም የደስታ እንባ ተናነቀን” በማለት ሁኔታውን ያስታውሳል። አዎን፣ ምሥራቹን ‘በትጋት’ መስበክ ታላቅ ደስታ ያስገኛል!

7 የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችና የዓለም ሁኔታዎች በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ጠልቀን እንደገባን ያመለክታሉ። የአምላክ ሕዝብ በሙሉ ሌሎች ምሥራቹን እንዲሰሙ ለማድረግ ‘የሚተጋበት’ ጊዜ አሁን ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ያለው ‘ድካም በጌታ ከንቱ እንደማይሆን’ ማረጋገጫ ሰጥቶናል።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 15:​58

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ