መጽሐፍ ቅዱስ —በሕይወትህ ውስጥ ያለው ኃይል የተባለው ቪዲዮ የነካችሁ እንዴት ነው?
ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች አማካኝነት ይህ ቪዲዮ ስለሚያስተላልፈው መልእክት በልብህ የሚሰማህን ግለጽ። (1ሀ) በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በጎ ለውጥ እንዲያደርጉ ኃይል የሰጣቸው ምንድን ነው? (ዕብ. 4:12) (1ለ) አንድ ሰው ይህን ኃይል ለማግኘትና በሕይወቱ ከዚህ ኃይል ለመጠቀም ምን ማድረግ ያስፈልገዋል? (2) የትዳር ጓደኛሞች (ሀ) በመካከላቸው ያለውን የሐሳብ ግንኙነት እንዲያሻሽሉ (ለ) ግልፍተኛ እንዳይሆኑ እንደሚረዷቸው የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? (3) በትዳር ረገድ ክርስቲያናዊ አመለካከትን ማዳበር የቤተሰብን ሕይወት የሚያሻሽለው እንዴት ነው? (ኤፌ. 5:28, 29) (4) ይሖዋ አምላክ ልጆች የሚፈልጓቸውን እንዲሁም የሚያስፈልጓቸውን ሦስት ነገሮች በመስጠት ረገድ ፍጹም ምሳሌ የተወልን እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ወላጆችም እንዲሁ ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? (ማር. 1:9-11) (5) ወላጆች በግላቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለልጆቻቸው ማስተማር የሚገባቸው ለምንድን ነው? እንዲህ በማድረግ ረገድ አዘውታሪ የመሆንን አስፈላጊነት የሚያሳየው ምንድን ነው? (ዘዳ. 6:6, 7) (6) ወላጆች የቤተሰብ ጥናት አስደሳች እንዲሆን ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? (7) መጽሐፍ ቅዱስን ከማስጠናት ሌላ የአምላክ ቃል ወላጆች ለልጆቻቸው ምን እንዲያደርጉ ያበረታታል? (8) የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ቤተሰቦች የሚገጥማቸውን የኢኮኖሚ ችግር እንዲቋቋሙ የሚረዳቸው እንዴት ነው? (9) ከሠራንባቸው የጤና ችግሮችን ለመቀነስ የሚረዱት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው? (10) በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙት መሠረታዊ ሥርዓቶች በሕይወትህ ውስጥ ለውጥ እንድታደርግ የረዱህ እንዴት ነው? (11) በአገልግሎት ላይ ያገኘኸው አንድ ሰው ይህንን ቪዲዮ መመልከቱ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ሊያበረታታው የሚችለው ለምን ሊሆን ይችላል?