የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በእንቅስቃሴ ላይ የተባለው ፊልም ታሪካዊ ቅኝት
በ1954 ተዘጋጅቶ እንደገና በቪዲዮ የቀረበውን ይህን ፊልም በምታዩበት ጊዜ የሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቡ:- (1) ይህ ፊልም በመጀመሪያ የተዘጋጀበት ዓላማ ምን ነበር? ምንስ አከናውኗል? (2) የይሖዋ ምሥክሮች የሚያዘጋጁዋቸው ጽሑፎች የትኞቹ ናቸው? ለማንና ለምን? (3) በአሁኑ ጊዜ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ስርጭት በ1954 ከነበረው ጋር ሲወዳደር ምን ይመስላል? (4) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኅትመት እንቅስቃሴያችን ይበልጥ ዘመናዊ እየሆነ የመጣው እንዴት ነው? (5) በ1953 በያንኪ ስታዲዮም ተደርጎ ከነበረው የአውራጃ ስብሰባ አንተን በጣም ያስገረመህ ምንድን ነው? (6) ትሬይለር ሲቲ የተባለው ምንድን ነው? ይህንንስ በሚመለከት የተገነዘብከው ምን አስደናቂ ነገር አለ? (7) ሥራችን በአንድ ብሔር ወይም ሕዝብ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ የሚያረጋግጠው ምንድን ነው? (8) የይሖዋ ድርጅት ሥራውን የሚያከናውንበትን ፍቅራዊ መንፈስ እንድታስተውል የረዳህ ነገር ምንድን ነው? (መዝ. 133:1) (9) የአዲሱ ዓለም ኅብረተሰብ በ1950ዎቹ ያደረገውን እንቅስቃሴ የሚያሳየውን ይህን ታሪካዊ ቅኝት ቢመለከት አድናቆት ያድርበታል ብለህ የምታስበው ማንን ነው?