ምሥክርነት ለመስጠት የሚረዱት የቪዲዮ ፊልሞች በሰዎች ላይ እያሳደሩ ያሉት በጎ ተጽዕኖ
1 “ልጃችን ገና መሄድ ሳይጀምር አንስቶ ይህንን የቪዲዮ ፊልም ሲያየው ቆይቷል። ደግሞ ደጋግሞ ይመለከተዋል። በልጆቻችን ልብ ውስጥ ለይሖዋ ፍቅር የሚያሳድሩ እንደዚህ ዓይነት መሣሪያዎች መኖራቸው እንዴት ግሩም ነው!” ይህች ክርስቲያን ወላጅ እየተናገረች ያለችው ስለ የትኛው የቪዲዮ ፊልም ነው? ኖኅ—አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ ስለተሰኘው የቪዲዮ ፊልም ነው። ልጅዋ ኖህ የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ሌላ ሰው ቤት የተመለከተ አንዲት ምሥክር ያልሆነች እናት ለአስተዋጽኦ 90 የአሜሪካ ዶላር ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው በመላክ ለልጆች የሚሆኑ ሌሎች የቪዲዮ ፊልሞች እንዳሉን ጠየቀች። የይሖዋ ድርጅት የሚያዘጋጃቸው የቪዲዮ ፊልሞች በወጣቶችም ሆነ በትልልቅ ሰዎች ላይ በጎ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው።
2 በቤተሰብ ውስጥ:- ምሥክር የሆነ አንድ ቤተሰብ የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተቋቁመዋል የተባለውን የቪዲዮ ፊልም ከተመለከተ በኋላ እናትየዋ እንዲህ አለች:- “ይሖዋ ተራ የሆኑ ሰዎች እጅግ ከባድ ሁኔታዎችን ተቋቁመው መጽናት እንዲችሉ እንዴት እንደረዳቸው ቀኑን ሙሉ ሳሰላስል ነበር! ስለዚያ ሁኔታ ማሰቡ ያሉብኝ ችግሮች ምን ያህል ከቁጥር የማይገቡ መሆናቸውን እንድገነዘብ አድርጎኛል። ይህንን የቪዲዮ ፊልም ከልጆቻችን ጋር መመልከታችን በይሖዋ ላይ የመመካትን አስፈላጊነት ይበልጥ እንዲገነዘቡ ረድቷቸዋል። ፊልሙን ካየን በኋላ ከሴት ልጆቻችን ጋር በፊልሙ ላይ በመወያየት ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ማንኛውም ዓይነት ተጽዕኖና ስደት ለመወጣት በተሻለ ሁኔታ የታጠቁ እንዲሆኑ ረድተናቸዋል።”
3 በትምህርት ቤት፦ አንድ ወጣት የይሖዋ ምሥክር በትምህርት ቤት ባቀረበው ሪፖርት ላይ በጽናት ተቋቁመዋል ከተባለው የቪዲዮ ፊልም ከፊሉን ለክፍሉ ተማሪዎች የማሳየት አጋጣሚ አገኘ። ቀደም ሲል መምህሯ የይሖዋ ምሥክሮችን እንደማትወድ ተናግራ ነበር። የቪዲዮ ፊልሙን ከተመለከተች በኋላ እንዲህ አለች:- “ይህ ፊልም ስለ ይሖዋ ምሥክሮች የነበረኝን አመለካከት ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። በሚቀጥለው ጊዜ ወደ ቤቴ ሲመጡ እንደምሰማቸውና ከእነሱ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንደምጀምር ቃል እገባለሁ!” ስለ እኛ የነበራትን አመለካከት የቀየረው ምንድን ነው? “እውነተኛ ፍቅራችንና ታማኝነታችን” እንደሆነ ተናግራለች።
4 በአገልግሎቱ:- አንዲት እህት ስለ እኛና ስለ እምነቶቻችን ጥያቄዎች ቢኖሯትም ጽሑፎች ለመውሰድ የማትፈልግ ሴት አጋጠመቻት። እህት ተመልሳ ስትሄድ የይሖዋ ምሥክሮች—ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ይዛ ሄደችና ለሴትዮዋና ለባሏ አሳየቻቸው። ሁለቱም በጥልቅ በመነካታቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተስማሙ። ጥሩ ምሥክርነት ስለ ተሰጣቸው ሕይወታቸውን ከአምላክ ፈቃድ ጋር አስማምተው መኖር ጀምረዋል።
5 የቪዲዮ ፊልሞቻችንን የሚገባውን ያህል እየተጠቀማችሁባቸው ነውን?