ልባዊ ምስጋና!
1 በሁሉም ሥፍራ ያሉ ክርስቲያን ቤተሰቦች የወጣቶች ጥያቄ —እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? ለተባለው ቪዲዮ ያላቸውን ልባዊ ምስጋና ገልጸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ አንድ አባት ወንዶች ልጆቹ ቪዲዮውን ከተመለከቱ በኋላ በጣም ከመነካታቸው የተነሳ በዝምታ እንደተዋጡና በቪዲዮው ላይ የታየው እያንዳንዱ ነገር የእነርሱ ሕይወት ነጸብራቅ እንደሆነ እንደተሰማቸው ተናግሯል! ከማላዊ የተገኘ አንድ ሪፖርት በዚያ የሚገኙ ወጣት ወንድሞችና እህቶች በትምህርት ቤት ካሉ የዕድሜ እኩዮቻቸው ተመሳሳይ የሆነ ተጽዕኖ ስለሚደርስባቸው በቀላሉ ከራሳቸው ሕይወት ጋር ማዛመድ እንደሚችሉ ገልጿል። በጀርመን የሚገኝ አንድ አባት ስለ ቪዲዮው ሲናገር “ለጸሎቴ መልስ እንዳገኘሁ ነው የምቆጥረው” ብሏል። አንዲት ወጣት “ይሖዋ ስለ እኔ እንደሚያስብ እንዳስታውስ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናችኋለሁ” ብላለች። በኒውዚላንድ የሚገኝ አንድ ሽማግሌ “ቪዲዮው በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ወጣቶቻችን መካከል አንዷ ወደ ሕይወት መንገድ እንድትመለስ ረድቷታል” ሲል ሪፖርት አድርጓል። አንዲት ባለ ትዳር ቪዲዮውን ከተመለከተች በኋላ እንዲህ ብላለች:- “በእውነት ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ወጣት ይህን ቪዲዮ ቢመለከትና እውነትን የራሱ ለማድረግ ቢነሳሳ በጣም ደስ ይለኛል!” ቤተሰቦች፣ ቪዲዮውን ለምን በድጋሚ አትመለከቱትም? ከዚያም ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው።
2 መግቢያ፦ እውነተኛ ጓደኛ ማለት ምን ማለት ነው?—ምሳሌ 18:24
3 ለጓደኝነት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች፦ የመገለል ስሜትን ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው? (ፊልጵ. 2:4) የባሕርይ ለውጥ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ያለብህ ለምንድን ነው? እንዲህ እንድታደርግ ማን ሊረዳህ ይችላል? ተጨማሪ ጓደኞች እንድታፈራ አጋጣሚውን የሚከፍትልህ ምንድን ነው? እነዚህን ጓደኞች ልታገኝ የምትችለውስ የት ነው?—2 ቆሮ. 6:13 NW
4 የአምላክ ወዳጅ መሆን፦ ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመስረት የምትችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጉ የሚክስ የሆነውስ ለምንድን ነው? (መዝ. 34:8) ከአምላክ ጋር ያለህን ወዳጅነት ይበልጥ ሊያጠነክሩልህ የሚችሉት እነማን ናቸው?
5 መጥፎ ጓደኞች፦ መጥፎ ጓደኞች ሊባሉ የሚችሉት እነማን ናቸው? (1 ቆሮ. 15:33) መጥፎ ጓደኞች አንድን ሰው ወደ መንፈሳዊ ውድቀት ሊመሩት የሚችሉት እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው የዲና ታሪክ ምን ትማራለህ?—ዘፍ. 34:1, 2, 7, 19
6 ዘመናዊ ድራማ፦ ታራ በብቸኝነት የተጠቃችው እንዴት ነበር? ከዓለማዊ ወጣቶች ጋር የነበራት ቅርርብ ምንም ጉዳት እንደሌለው ለማሳመን የሞከረችው እንዴት ነው? እነዚህ ጓደኞቿ ለምን ዓይነት አደጋዎች እንድትጋለጥ አደረጓት? ወላጆቿ የነበረችበትን አደገኛ ሁኔታ ለመመልከት ያልቻሉት ለምን ነበር? ሆኖም በመንፈሳዊ እንድታገግም የረዷት በምን ዓይነት ዝንባሌ ነበር? አንዲት አቅኚ እህት ለታራ እውነተኛ ጓደኛ ልትሆንላት የቻለችው እንዴት ነው? ክርስቲያኖች በምሳሌ 13:20 እና በኤርምያስ 17:9 ላይ የሚገኘውን ምክር መከተል ያለባቸው ለምንድን ነው? ታራ ምን ጠቃሚ ትምህርት አገኘች?
7 መደምደሚያ፦ ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርቶችን አግኝተሃል? ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልትጠቀምበት ትችላለህ?—መዝ. 71:17