የወጣቶች ጥያቄ —እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ የሰው ልጆችን ሲፈጥር የሐሳብ ግንኙነት ማድረግ እንዲሁም ጓደኝነት መመሥረት እንዲችሉ አድርጎ ነው። (ምሳሌ 17:17፤ 18:1, 24) እንዲህ ያለው ጓደኝነት ለሁለቱም ወገኖች ጥቅም እንዲያስገኝ ጓደኞቻችንን በጥበብ መምረጥ ይኖርብናል። (ምሳሌ 13:20) የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ።
መግቢያ፦
(1) እውነተኛ ጓደኛ ማለት ምን ማለት ነው?
ለጓደኝነት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች፦
(2) የመገለልን ስሜት ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው? (ፊልጵ. 2:4) (3) ባሕሪያችንን ለማሻሻል ፈቃደኛ መሆን ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ለማድረግስ ማን ሊረዳን ይችላል? (2 ቆሮ. 13:11) (4) ተጨማሪ ጓደኞች ለማፍራት የሚያስችሉን ምን አጋጣሚዎች አሉ?—2 ቆሮ. 6:13
የአምላክ ወዳጅ መሆን፦
(5) ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረግ የሚክስ የሆነው ለምንድን ነው? (መዝ. 34:8) (6) ይሖዋን የቅርብ ወዳጃችን ስናደርገው ጥሩ ጓደኞችን ማፍራት የምንችለው እንዴት ነው?
መጥፎ ጓደኞች፦
(7) መጥፎ ጓደኞች ሊባሉ የሚችሉት እነማን ናቸው? (1 ቆሮ. 15:33) (8) መጥፎ ጓደኞች አንድን ሰው ወደ መንፈሳዊ ውድቀት ሊመሩት የሚችሉት እንዴት ነው?
ዘመናዊ ድራማ፦
(9) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው የዲና ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘፍ. 34:1, 2, 7, 19) (10) ታራ ከማያምኑ ወጣቶች ጋር የነበራት ቅርርብ ምንም ጉዳት እንደሌለው ለማሳመን የሞከረችው እንዴት ነው? (11) የታራ የትምህርት ቤት ጓደኞች ለምን ዓይነት አደጋዎች እንድትጋለጥ አደረጓት? (12) የታራ ወላጆች የነበረችበትን አደገኛ ሁኔታ ማስተዋል ያልቻሉት ለምን ነበር? ሆኖም በመንፈሳዊ እንድታገግም የረዷት ምን ዓይነት ዝንባሌ ይዘው ነው? (13) አንዲት አቅኚ እህት ለታራ እውነተኛ ጓደኛ የሆነቻት እንዴት ነው? (14) ታራ አመለካከቷ የተቀየረው እንዴት ነው?
መደምደሚያ፦
(15) ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርት አግኝተሃል? (16) ይህን ቪዲዮ ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልትጠቀምበት ትችላለህ?
ካሉን ዝምድናዎች ሁሉ የላቀውን ይኸውም ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና ጠብቀን ለመኖር የሚረዱን ጓደኞችን እንምረጥ።—መዝ. 15:1, 4፤ ኢሳ. 41:8