ለመላው የወንድማማች ማኅበራችን ፍቅር የምናሳይበት ምክንያት
በዚህ ፍቅር በጠፋበት ዓለም ውስጥ መንፈሳዊ ወንድሞቻችንን ከልብ መውደድ የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጴጥ. 2:17 NW ) በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ እውነተኛ ፍቅር እንዳለ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (ማቴ. 23:8) መላው የወንድማማች ማኅበር የተባለውን የቪዲዮ ፊልም በመጠቀም ይህን ማድረግ እንችላለን። እርስ በርስ የምንዋደድበትን ምክንያት ይህ ቪዲዮ ያሳያል። ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ትችላለህ?
(1) ዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን የሚያከናውናቸው ሦስት እንቅስቃሴዎች ምንድን ናቸው? (2) ወንድሞቻችን (ሀ) ርቆ በሚገኘው በአላስካ ምድር (ለ) በአውሮፓ ትላልቅ ወደቦችና (ሐ) በፔሩ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች ውስጥ ምሥራቹን በጽናት እየሰበኩ ያሉት እንዴት ነው? (3) ምሥክርነቱን ለመስጠት ውጤታማ ሆኖ የተገኘው መሣሪያ የትኛው ነው? (4) ምሥራቹን መስበክ እንዲያው ተራ ሥራ እንደሆነ አድርገን ማሰብ የማይገባን ለምንድን ነው? (5) የይሖዋ ምሥክሮች እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ ዓውሎ ነፋስና የእርስ በርስ ጦርነት የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ አንዳቸው ለሌላው እርዳታና ማጽናኛ እንደሰጡ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ተናገር። (በነሐሴ 22, 1995 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 23 ላይ ታካኦ የተባለ ወንድም የሰጠውን ሐሳብና በጥቅምት 22, 1996 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 20 ላይ ኮቶዮ የተናገረችውን ሐሳብ ተመልከት።) (6) ሁላችንም የክርስቲያን ወንድማማች ማኅበራችንን ለይቶ የሚያሳውቀውን ጉልህ ምልክት በየትኞቹ ተግባራዊ መንገዶች ማሳየት እንችላለን? (ዮሐ. 13:35) (7) የጉባኤ ስብሰባዎቻችንን ምን ያህል ከፍ አድርገን መመልከት አለብን? (8) ከዚህ በፊት መሰብሰቢያ ያልነበራቸው ወንድሞች የመንግሥት አዳራሽ ሲያገኙ ምን ተሰማቸው? (9) በምሥራቅ አውሮፓና በሩሲያ የሚገኙ ወንድሞቻችን በእገዳ ሥር በነበሩበት ጊዜ መንፈሳዊነታቸውን ጠብቀው መኖር የቻሉት እንዴት ነው? (10) በአሁኑ ጊዜም ብዙ አስፋፊዎች በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ምን የሚደነቁ ጥረቶችን ያደርጋሉ? ለምንስ? ይህስ ምን እንድታደርግ ያበረታታሃል? (11) በአንድነት አምላክን እንድታመልክ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት ሌሎችን እንድትረዳና ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምስክርነቱን እንድትሰጥ የሚገፋፋህ ምንድን ነው? (12) የዚህን የቪዲዮ ፊልም የግል ቅጂ ማግኘታችንና ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ሁሉ ለማሳየት ጥረት ማድረጋችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?