የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/03 ገጽ 9
  • በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ማበረታቻ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ማበረታቻ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የቀዘቀዙትን አትርሷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • “ወደ እኔ ተመለሱ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ሳይዘገዩ እንዲመለሱ እርዷቸው!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 2/03 ገጽ 9

በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ማበረታቻ

1 ሐዋርያው ጴጥሮስ የእምነት አጋሮቹ ማበረታቻ እንደሚያስፈልጋቸው በተገነዘበ ጊዜ በአሳቢነት ተነሳስቶ ፍቅራዊ ማሳሰቢያና ማበረታቻ ሰጥቷቸዋል። (2 ጴ⁠ጥ. 1:​12, 13፤ 3:​1) ጴጥሮስ ‘እምነት ያገኙትን’ ‘በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳይሆኑ’ መንፈሳዊ ባሕርያትን ማዳበራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧቸዋል። (2 ጴ⁠ጥ. 1:​1, 5-8) የጴጥሮስ ዓላማ የእምነት አጋሮቹ ‘ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆነው በሰላም በመገኘት’ በይሖዋ መጠራታቸውንና መመረጣቸውን እንዲያረጋግጡ መርዳት ነበር። (2 ጴ⁠ጥ. 1:​10, 11፤ 3:​14) ለብዙዎቹ ክርስቲያኖች ይህ በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ማበረታቻ ነበር።

2 በዛሬው ጊዜም ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ለአምላክ ሕዝቦች ተመሳሳይ አሳቢነት ያሳያሉ። በዚህ “የሚያስጨንቅ ዘመን” በርካታ የይሖዋ አገልጋዮች ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እየታገሉ ይኖራሉ። (2 ጢ⁠ሞ. 3:1) አንዳንዶች ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሱ በሚሄዱ የኢኮኖሚ፣ የቤተሰብ ወይም የግል ችግሮች የተነሳ “ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፣ ማየትም ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፣ ልቤም ተወኝ” በማለት እንደተናገረው እንደ ዳዊት ይሰማቸው ይሆናል። (መዝ. 40:12) እነዚህ ክርስቲያኖች ተጽዕኖዎቹ በጣም ሲደራረቡባቸው ወሳኝ የሆኑ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ችላ ሊሉና በክርስቲያናዊ አገልግሎት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ሊያቋርጡ ይችላሉ። ሆኖም ግን የይሖዋን ‘ትእዛዛት አልረሱም።’ (መዝ. 119:176) በዚህ ጊዜ የሽማግሌዎች ድጋፍና ማበረታቻ ወሳኝ ነው።​—⁠ኢሳ. 32:1, 2

3 ለዚህም ሲባል ሽማግሌዎች በስብከቱ ሥራ መካፈል ያቆሙትን ለመርዳት ልዩ ጥረት እንዲያደርጉ ተበረታተዋል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት የተጠናከረ ጥረት በመደረግ ላይ ሲሆን እንቅስቃሴው እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ድረስ ይዘልቃል። የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቾች አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎች ከጉባኤው ጋር እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲጀምሩ ለመርዳት ቤታቸው ሄደው በመንፈሳዊ እንዲያበረታቷቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ግለሰቡን በግል መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ዝግጅት ማድረግ የሚቻል ሲሆን ሌሎች አስፋፊዎችም በዚህ ረገድ እርዳታ እንዲያደርጉ ሊጠየቁ ይችላሉ። አንተም እገዛ እንድታበረክት ከተጠየቅህ በደግነትና ማስተዋል በተሞላበት መንገድ ማበረታቻ በመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላለህ።

4 አገልግሎት አቁሞ የነበረ አንድ አስፋፊ ከጉባኤው ጋር እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀምር ሁላችንም እንደሰታለን። (ሉቃስ 15:6) አገልግሎት ያቆሙትን ለማበረታታት የምናደርገው ጥረት ‘በጊዜው የተነገረ ቃል’ የሚኖረውን መልካም ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን እንመኛለን።​—⁠ምሳሌ 25:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ