የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/03 ገጽ 1
  • ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ መስበክ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ መስበክ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዎችን ፍላጎት ለመቀስቀስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተጠቀሙ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • የመንግሥት ስብከታችንን ለማሻሻል የምንችልባቸው መንገዶች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ዝግጅት በማድረግ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኞች ናችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 6/03 ገጽ 1

ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ መስበክ

1 ዛሬ በዓለማችን ላይ በአንድ ጀምበር ብዙ ነገሮች ይለዋወጣሉ። የተፈጥሮ አደጋ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም ከባድ አደጋ ድንገት ሊከሰት ይችላል። ሰዎችን የሚያሳስቧቸው ነገሮችም በዚያው መጠን በፍጥነት ይለዋወጣሉ። (ሥራ 17:21፤ 1 ቆ⁠ሮ. 7:31) በዚህ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

2 ሰዎች የሚያሳስቧቸውን ነገሮች ማስተዋል:- ሰዎች ጆሯቸውን እንዲሰጡን ማድረግ የምንችልበት አንዱ መንገድ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መክፈት ነው። በአንድ ወቅት ኢየሱስ አድማጮቹ በአምላክ ፊት ስላላቸው አቋም በቁም ነገር እንዲያስቡበት ለማሳሰብ ሰዎቹ የሚያውቋቸውን በወቅቱ የተፈጸሙ አሳዛኝ ክስተቶች ጠቅሶ ነበር። (ሉቃስ 13:1-5) እኛም በተመሳሳይ ምሥራቹን ስንሰብክ በክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች የሚያሳስቧቸውን ወቅታዊ ጉዳዮች መጥቀስ እንችላለን። ሆኖም በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ በምንወያይበት ጊዜ በፖለቲካዊ ወይም በማኅበራዊ ጉዳዮች ረገድ የአንድ ወገን ደጋፊ ሆነን እንዳንገኝ መጠንቀቅ ይኖርብናል።​—⁠ዮሐ. 17:16

3 በወቅቱ ሰዎችን እያሳሰባቸው ያለው ነገር ምን እንደሆነ እንዴት ማወቅ እንችላለን? ምናልባትም ከሁሉ የተሻለው ዘዴ ጥያቄ መጠየቅና የሚሰጡትን መልስ በጥሞና ማዳመጥ ነው። (ማቴ. 12:34) ለሰዎች ያለን አሳቢነት አመለካከታቸውን ለማስተዋልና በዘዴ ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ልባቸው ውስጥ ያለውን አውጥተው እንዲናገሩ ለማድረግ እንድንጥር ይገፋፋናል። የምናነጋግረው ሰው በአጋጣሚ የሚሰነዝረው ሐሳብ በዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎችን የሚያሳስባቸው ነገር ምን እንደሆነ የሚጠቁምና በዚያ መሠረት ምሥክርነት ለመስጠት አጋጣሚ የሚከፍት ሊሆን ይችላል።

4 መግቢያ ማዘጋጀት:- በዚህ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ አገልግሎት ወጥተን ሰዎችን ለማነጋገር በምንዘጋጅበት ጊዜ ማመራመር በተባለው መጽሐፍ መጠቀም እንችላለን። በመግቢያችን ላይ ወቅታዊ ሐሳቦችን እንዴት መጠቀም እንደምንችል ለማወቅ ከገጽ 10 እስከ 11 ላይ “ወንጀል/ደህንነት” እና “ወቅታዊ የዓለም ሁኔታዎች” በሚሉት ርዕሶች ሥር ያሉትን ሐሳቦች መመልከት እንችላለን። በመስከረም 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 ላይም ተመሳሳይ ሐሳቦችን ማግኘት ይቻላል። መግቢያ በምትዘጋጁበት ጊዜ ከሐሳቡ ጋር የሚሄድ ተስማሚ ጥቅስ መምረጥ እንዳለባችሁ አትዘንጉ።

5 በክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች በየጊዜው የሚያሳስቧቸውን የተለያዩ ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት ምሥራቹን በዚያ መሠረት ለማቅረብ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ መንገድ ሰዎችን በወቅቱ ስለሚያሳስባቸው ጉዳይ ልናወያያቸው እንችላለን። እንዲህ በማድረግ ብዙ ሰዎች የማይለዋወጡ ባሕርያትና የሥነ ምግባር ደምቦች ያሉትን አምላክ እንዲያውቁት ልንረዳቸው እንችላለን።​—⁠ያዕ. 1:17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ