የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ባሉበት ክልል ውስጥ ጽሑፎችን ማበርከት
1. ብዙ ጉባኤዎች በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ለምንድን ነው?
1 በብዙ ቦታዎች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ሰዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ እውነትን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ ትምህርቱ የሚቀልላቸው ከመሆኑም በላይ ይበልጥ በጥልቀት ይረዱታል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በቀላሉ በሚረዱት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች እንዲያገኙ የሚያስችል ምን ዝግጅት አለ?
2. በተለያየ ቋንቋ የሚካሄዱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጉባኤዎች በተመሳሳይ ክልል ውስጥ የሚያገለግሉ ከሆነ ምን ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል?
2 ጽሑፎች ማበርከት ያለብን መቼ ነው? በተለያየ ቋንቋ የሚካሄዱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጉባኤዎች በተመሳሳይ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ያገለግሉ ይሆናል። በዚህ ጊዜ የጉባኤዎቹ የሽማግሌዎች አካላት በእያንዳንዱ ቋንቋ የተሟላ ምሥክርነት መስጠት እንዲቻል በአገልግሎት የበላይ ተመልካቾቻቸው አማካኝነት ለሁሉም ጉባኤዎች ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ያደርጋሉ። አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤት በሚያገለግሉበት ጊዜ ሌላው ጉባኤ(ዎች) በሚጠቀምበት ቋንቋ ጽሑፎች ከማበርከት ይቆጠባሉ። ይሁን እንጂ አስፋፊዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወይም ከመንገድ ወደ መንገድ ሲያገለግሉ በተለያየ ቋንቋ ጽሑፎች ማበርከት ይችላሉ።—የጥቅምት 1990 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
3. አንድ ጉባኤ በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎች ሊኖረው የሚገባው መቼ ነው?
3 ጉባኤዎች በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎች ሊኖሯቸው የሚገባው መቼ ነው? በአንድ አካባቢ የውጭ አገር ቋንቋ የሚናገሩ በርከት ያሉ ሰዎች ቢኖሩም በዚህ ቋንቋ የሚካሄድ ጉባኤ በማይኖርበት ጊዜ ምን ማድረግ ይቻላል? በዚህ ጊዜ ጉባኤዎች ትራክቶችን፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው እና የአምላክ ወዳጅ የተባሉትን ብሮሹሮች እንዲሁም እውቀት መጽሐፍን የመሳሰሉ በዚያ ቋንቋ የሚገኙ መሠረታዊ ጽሑፎችን በተወሰነ መጠን መያዝ ይችላሉ። አስፋፊዎች በዚያ ቋንቋ የተዘጋጀ ጽሑፍ ማንበብ የሚችል ሰው በሚያገኙበት ጊዜ ጽሑፎቹን ሊያበረክቱለት ይችላሉ።
4. በጉባኤው ውስጥ የማይገኙ በሌላ ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎችን ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
4 ጽሑፎች ማዘዝ የሚቻለው እንዴት ነው? ፍላጎት ያሳየ ሰው ማንበብ በሚችለው ቋንቋ የተዘጋጀ ጽሑፍ በጉባኤው ውስጥ ከሌለ በዚያ ቋንቋ ጽሑፍ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? አስፋፊው በዚያ ቋንቋ የትኞቹ ጽሑፎች በጉባኤው ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ የጽሑፍ አገልጋዩን ማነጋገርና የሚፈልጋቸው ጽሑፎች በቀጣዩ የጉባኤው የጽሑፍ ትእዛዝ ላይ እንዲካተቱለት መጠየቅ ይኖርበታል።
5. ከመደበኛው የጉባኤው ትእዛዝ ውጪ ጽሑፍ በአስቸኳይ ማግኘት ካስፈለገ ምን ማድረግ ይቻላል?
5 አስፋፊው ጽሑፉ በቶሎ እንዲደርሰው የሚፈልግ ከሆነ ጉባኤው በፕሮግራሙ መሠረት ቀጥሎ ከሚልከው የጽሑፍ ትእዛዝ በፊት ትእዛዙ ሊላክለት ይቻል እንደሆነ ለማወቅ ከጉባኤ የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት አንዱን መጠየቅ ይችላል። ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ የጽሑፍ አስተባባሪው ወይም እርሱ የወከለው ሰው ጽሑፉ በአስቸኳይ እንዲላክላቸው በፖስታ ወይም በስልክ ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ይችላሉ። ጽሑፉ በጉባኤው ቋሚ አድራሻ ወይም አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ በጊዜያዊ አድራሻ ይላክላቸዋል።
6. ክርስቲያናዊ ጽሑፎችን ለሰዎች የምናበረክትበት ዓላማ ምንድን ነው?
6 ቋንቋቸው ምንም ይሁን ምን ‘ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ’ ለመርዳት በክርስቲያናዊ ጽሑፎቻችን ጥሩ አድርገን እንጠቀምባቸው።—1 ጢሞ. 2:3, 4