መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት እንችላለን?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ለችግረኞች የተዋጣ ገንዘብ አላግባብ እንደሚባክን የሚጠቁሙ ዘገባዎች አንዳንዶች ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች መስጠታቸው ስላለው ጠቀሜታ ጥርጣሬ እንዲፈጠርባቸው አድርጓል። በአንጻሩ ደግሞ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል። ታዲያ ምን ቢደረግ የተሻለ ነው ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ዕብራውያን 13:16ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ስላለው ልግስና ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ 2003
“ብዙ ወጣቶች ለአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ተዳርገው ሕይወታቸውን ማበላሸታቸው አያሳዝንም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አብዛኛውን ጊዜ ችግሩ የሚጀምረው ወጣቶች ከመጥፎ ልጆች ጋር ሲገጥሙ ነው። [1 ቆሮንቶስ 15:33ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ወጣቶች ዕፅ መውሰድ እንዲጀምሩ የሚገፋፋቸውን ምክንያትና ወላጆች እነርሱን ከአደጋ ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“አንዳንዶች ኢየሱስ በታሪክ ዘመናት ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ሰው እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች ግን በምድር ላይ መኖሩን እንኳ ይጠራጠራሉ። ስለ እርሱ የፈለግነውን ብናምን ለውጥ ያመጣል? [መልሱን ካዳመጥህ በኋላ ሥራ 4:12ን አንብብ።] ኢየሱስ በምድር ላይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ምን ማስረጃ አለ? ይህ መጽሔት ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
June 22
“ብዙ ሰዎች በተፈጥሮ ሀብት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ያሳስባቸዋል። በሐሩር ክልል ውስጥ የሚገኙት ደኖች ተጠብቀው እንዲቆዩ ማድረግ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በሐሩር ክልል ውስጥ የሚገኙ ደኖችን ከጥፋት ለመታደግ በአሁኑ ጊዜ እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች ይገልጻል። ከዚህም በላይ አምላክ የሰጠው የሚከተለው ግሩም ተስፋ እንዴት እንደሚፈጸም ያብራራል።” ኢሳይያስ 11:9ን አንብብ።