መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“አንዳንድ ሃይማኖታዊ መሪዎች የሰብዓዊውን ኅብረተሰብ ሕይወት ለማሻሻል በሚል በፖለቲካ ጉዳዮች ይካፈላሉ። ከዚህ በተቃራኒ ኢየሱስ ሰዎች ሊያነግሱት በፈለጉ ጊዜ ምን እንዳደረገ ልብ ይበሉ። [ዮሐንስ 6:15ን አንብብ።] ኢየሱስ ትኩረት ያደረገው ለሰዎች ዘላቂ ጥቅም በሚያስገኘው ነገር ላይ ነበር። ይህ መጽሔት ዘላቂው መፍትሔ ምን እንደሆነ ይገልጻል።”
ንቁ! ግንቦት 2004
“ብዙዎች በሥራ ቦታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። አንዳንዶቹም በሥራ ባልደረቦቻቸው ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ያሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት የሚያስችል ምክር እንደሚሰጥ ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 15:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በሥራ ቦታችን ከሌሎች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ለማድረግ የሚረዱን ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦች ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“ሰዎች በምድር ላይ የሚያደርጓቸው ነገሮች በአምላክ ስሜት ላይ ለውጥ ያመጡ እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ ጥቅስ የምናደርጋቸው ነገሮች አምላክን ሊያስደስቱት እንደሚችሉ ያሳያል። [ምሳሌ 27:11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክን ልብ ደስ ያሰኙ ሰዎችን ምሳሌ የሚጠቅስ ከመሆኑም በላይ እኛም እንደዚህ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።”
Awake! May 22
“የሕክምናው ሳይንስ በሽታን በመዋጋት ረገድ አስደናቂ እድገት አድርጓል፤ ሆኖም በሽታ ከዓለም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚወገድበትን ጊዜ ለማየት የምንታደል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በኢሳይያስ 33:24 ላይ ያለው ትንቢት ሲፈጸም በምድር ላይ የሚኖር ሁሉ የተሟላ ጤንነት እንደሚኖረው ይናገራል።” [ከዚያም ጥቅሱን አንብብ።]