የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/06 ገጽ 6
  • ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በምሽት አገልግሎት መካፈል ትችላላችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • በምሽት ምሥክርነት ለመካፈል ሞክርሃል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • የሚገባቸውን ሰዎች መፈለግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • በአገልግሎት የምታሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 4/06 ገጽ 6

ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?

1. የአገልግሎት ፕሮግራማችንን ማስተካከል ያለብን ለምንድን ነው?

1 እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን “ሰዎችን አጥማጆች” እንድንሆን የቀረበልንን ግብዣ ተቀብለናል። (ማቴ. 4:19) ልክ እንደ ዓሣ አጥማጆች፣ ሰዎች ቤታቸው በሚገኙበት ጊዜ ለመስበክ ፕሮግራማችንን ካስተካከልን ሰዎችን በማጥመዱ ሥራ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን። አመሻሹ ላይ ብዙ ሰዎች በቤታቸው ይገኛሉ። ብዙውን ጊዜ ሰዎች በዚህ ሰዓት ይበልጥ ስለሚረጋጉ እንግዳ ለመቀበል ፈቃደኞች ይሆናሉ። በዚህ ጊዜ ለመስበክ ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?—1 ቆሮ. 9:23

2. ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ለማዳረስ የሚያስችሉን አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

2 የምሽት አገልግሎት:- በምሽት ለማገልገል ቀደም ብለን እቅድ ካወጣን ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ማዳረስ እንችላለን። (ምሳሌ 21:5) ወጣቶች ከትምህርት ቤት በኋላ ሌሎች ደግሞ ከሥራ መልስ መስበክ ይችሉ ይሆናል። አንዳንድ የመጽሐፍ ጥናት ቡድኖች ከሳምንታዊ ስብሰባቸው አንድ ሰዓት ቀደም ብለው ለመስበክ ዝግጅት ማድረግ ይችላሉ።

3. በክልልህ ውስጥ አመሻሹ ላይ ለመስበክ በየትኞቹ መንገዶች መጠቀም ትችላለህ?

3 አመሻሹ ላይ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መስበክ በሌላ ጊዜ ቤታቸው የማይገኙትን ሰዎች ለማነጋገር ያስችላል። በብዙ ክልሎች ውስጥ ምሽት ላይ ከመንገድ ወደ መንገድ ማገልገልና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች መካፈል ይቻላል። ተመላልሶ ለመጠየቅም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ብዙዎች ምሽት ላይ መሄዱን አመቺ ሆኖ አግኝተውታል።

4. በምሽት ስናገለግል አስተዋይና አሳቢ መሆናችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

4 አስተዋዮች መሆን:- በምሽት ስናገለግል አስተዋይ መሆን ያስፈልጋል። ብዙውን ጊዜ ባለቤቶቹ ለመተኛት በሚዘጋጁበት ሰዓት ቤታቸው ከመሄድ ይልቅ ቀደም ብለን አገልግሎታችንን ብናቆም ጥሩ ነው። (ፊልጵ. 4:5 NW) በሩን ስታንኳኳ ልትታይ በምትችልበት ቦታ ቁም፤ እንዲሁም ራስህን በግልጽ አስተዋውቅ። የመጣህበትን ዓላማ ቶሎ ብለህ ተናገር። ቤታቸውን ያንኳኳኸው አጉል ሰዓት ላይ ከሆነ፣ ለምሳሌ ቤተሰቡ ምግብ እየተመገበ ቢሆን ሌላ ጊዜ እንደምትመጣ ንገራቸው። ምንጊዜም ቢሆን አሳቢ ሁን።—ማቴ. 7:12

5. በምንሰብክበት ጊዜ አደጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ሁኔታዎች መራቅ የምንችለው እንዴት ነው?

5 አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮች እንዳሉ መገንዘብም ይኖርብናል። እምብዛም ብርሃን በሌለበት አካባቢ የምታገለግል ከሆነ አደገኛ እንዳልሆኑ በምታስባቸው ቦታዎች ላይ ብቻ አገልግል። ከጨለመ በኋላ ወደሚያሰጉ ቦታዎች አትሂድ።—ምሳሌ 22:3

6. በምሽት ማገልገል ምን ተጨማሪ ጥቅም አለው?

6 በምሽት ማገልገል በጉባኤ ውስጥ ካሉት ረዳትና የዘወትር አቅኚዎች ጋር ለማገልገል ያስችለናል። (ሮሜ 1:12) በዚህ ዓይነቱ የአገልግሎት ዘርፍ ለመሳተፍ ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ