የጥያቄ ሣጥን
◼ የግላችንን የኢሜይል አድራሻ በምናሰራጫቸው ጽሑፎች ላይ መለጠፋችን ተገቢ ነው?
አንዳንድ አስፋፊዎች የራሳቸውን የኢሜይል አድራሻ በማኅተም በማስቀረጽ ለሰዎች በሚያበረክቷቸው መጽሔቶችና ትራክቶች ላይ ያትማሉ ወይም በወረቀት አዘጋጅተው በጽሑፎቹ ላይ ይለጥፋሉ። ይህም ጽሑፉን የተቀበሉት ሰዎች ተጨማሪ መረጃ በሚፈልጉበት ጊዜ አስፋፊውን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላቸዋል። ፍላጎት ያሳዩትን ለመርዳት የሚደረጉት እነዚህ ጥረቶች በቅን ልቦና የሚደረጉ ናቸው። ነገር ግን የይሖዋ ምሥክሮች ድረ ገጽ በመጽሔቶችና በትራክቶች ጀርባ ላይ ይገኛል። በመሆኑም የግል የኢሜይል አድራሻችንን በምናበረክታቸው ጽሑፎች ላይ ባንለጥፍ የተሻለ ነው።
አንድ አስፋፊ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በተለይ ተመላልሶ መጠየቅ በሚያደርግበት ጊዜ የሚገኝበትን አድራሻ በወረቀት ላይ ጽፎ መስጠት አለመስጠት የግሉ ውሳኔ ነው። ጽሑፍ ያበረከትንላቸው ሰዎች ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ እነሱ እስኪያነጋግሩን ድረስ ከመጠበቅ ይልቅ ፍላጎት ያሳዩትን ተመልሰን ለመጠየቅ እኛው ራሳችን ቅድሚያውን መውሰድ ይገባናል። ግለሰቡ ፍላጎት ያለው መሆን አለመሆኑን ይበልጥ ማወቅ የምንችለው ፊት ለፊት በምንነጋገርበት ጊዜ ነው።