እባካችሁ ወዲያውኑ ሄዳችሁ አነጋግሯቸው
እነማንን? ጽሑፍ እንዲላክላቸው ወይም በየጊዜው መጽሔት እንዲመጣላቸው አሊያም አንድ የይሖዋ ምሥክር ቤታቸው መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎችን ነው። እነዚህ ሰዎች ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡት እንዴት ነው? ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ደብዳቤ በመጻፍ ወይም ስልክ በመደወል አሊያም በኢንተርኔት አድራሻችን አማካኝነት የሚፈልጉትን ነገር በመጠየቅ ነው። ቅርንጫፍ ቢሮው ፍላጎት ካላቸው ሰዎች እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ሲቀርብለት S-70 (“እባክህ ይህንን ሰው ብቁ የሆነ አስፋፊ እንዲያነጋግረው አድርግ”) በተባለው ቅጽ አማካኝነት ግለሰቡ ባለበት አካባቢ ለሚገኝ ጉባኤ ጉዳዩን ያሳውቃል። ሽማግሌዎች S-70 የተባለው ቅጽ ሲደርሳቸው ቅጹን ፍላጎት ያሳየውን ሰው በትጋት ተከታትሎ ለሚረዳ አስፋፊ ወዲያውኑ መስጠት አለባቸው። አስፋፊው ግለሰቡን ቤቱ ሄዶ ማግኘት ካቃተው በስልክ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ወይም ትኩረት በማይስብ መልኩ ማስታወሻ ትቶለት መሄድ ይችላል። ፍላጎት ያለውን ሰው እንድታነጋግር አድራሻ ከተሰጠህ እባክህ ወዲያውኑ ከግለሰቡ ጋር ለመገናኘት የቻልከውን ሁሉ አድርግ።