የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/11 ገጽ 2
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወዲያውኑ ተከታትላችሁ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • እባካችሁ ወዲያውኑ ሄዳችሁ አነጋግሯቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ምን ዓይነት ሥራ ይከናወናል?
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
km 11/11 ገጽ 2

የጥያቄ ሣጥን

◼ በጽሑፎቻችን የመጨረሻ ገጽ ላይ የሚገኙ ኩፖኖችን ወይም ቅጾችን እንዲሁም በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ መጠይቆችን መሙላት ያለበት ማን ነው?

ተጨማሪ ጽሑፍ ማግኘት ወይም የይሖዋ ምሥክሮች መጥተው እንዲያነጋግሯቸው የሚፈልጉ አንባቢዎች ሞልተው ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው የሚልኳቸው ኩፖኖች በጽሑፎቻችን ላይ ይወጣሉ። ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰው www.watchtower.org በተባለው ድረ ገጻችን አማካኝነት የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስጠኑት መጠየቅ ይችላል። እነዚህ ዝግጅቶች ብዙ ሰዎች እውነትን የመማር አጋጣሚ እንዲያገኙ ረድተዋቸዋል። ይሁንና ከተሞክሮ ማየት እንደሚቻለው አስፋፊዎች ዘመዶቻቸው ወይም ሌሎች ሰዎች ጽሑፎች እንዲያገኙ አሊያም አንድ የይሖዋ ምሥክር ሄዶ እንዲያነጋግራቸው ካላቸው ጉጉት የተነሳ እነዚህን ኩፖኖች ሞልተው ሲልኩ ችግሮች ይፈጠራሉ።

ምንም ጥያቄ ሳያቀርቡ ከቅርንጫፍ ቢሮው ጽሑፍ የተላከላቸው አንዳንድ ሰዎች ድርጅቱ አድራሻቸውን መዝግቦ በመያዝ ጽሑፎች እየላከ እንዳማረራቸው ስለተሰማቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል። እንዲህ ያሉ ግለሰቦችን ተከታትለው እንዲረዱ የሚገልጽ ማስታወሻ የደረሳቸው አስፋፊዎች ግለሰቡ ሲናደድ በማየታቸው በጣም ግራ ተጋብተዋል። በመሆኑም በድረ ገጻችን ላይ የሚገኙ መጠይቆችን ወይም ኩፖኖችን መሙላት የሚኖርባቸው ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ራሳቸው እንጂ አስፋፊዎች አይደሉም። ቅርንጫፍ ቢሮው ኩፖኖቹ ለሌሎች ሰዎች የተሞሉ መሆናቸውን ካወቀ ጥያቄውን አያስተናግድም።

ታዲያ ዘመዶቻችንን ወይም የምናውቃቸውን ሰዎች በመንፈሳዊ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? ጽሑፎች እንዲያገኝ ከፈለግን እኛ ራሳችን በስጦታ መልክ በቀጥታ ልንልክለት እንችላለን። ግለሰቡ የበለጠ ለማወቅ ካለው ፍላጎት የተነሳ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲያነጋግሩት ይፈልግ ይሆናል፤ ይሁንና የሚኖርበትን አካባቢ ሽማግሌዎች፣ እንዴት ማግኘት እንደምንችል የማናውቅ ከሆነ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለው ቅጽ ሞልተን ለጉባኤያችን ጸሐፊ መስጠት እንችላለን፤ ጸሐፊው ቅጹን በሚገባ ከተመለከተ በኋላ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ይልከዋል። ይሁን እንጂ ፍላጎት ያሳየው ግለሰብ በእስር ቤት፣ በማረሚያ ቤት ወይም በሆስፒታል የሚገኝ ከሆነ እሱን ወክላችሁ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መጻፍ የለባችሁም። ከዚህ ይልቅ እዚያ አካባቢ የሚያገለግሉ ወንድሞችን እንዲያነጋግር አሊያም ግለሰቡ ራሱ ለቅርንጫፍ ቢሮው እንዲጽፍ ልታበረታቱት ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ