የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/08 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን–1

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን–1
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ ጥናት ለመምራት ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ—መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የምንጠቀምበት ዋነኛ ጽሑፍ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እንዲታዘዙ እርዳ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 1/08 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን–1

◼ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን ልናስጠናቸው የሚገቡን ሁለት ጽሑፎች የትኞቹ ናቸው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመርም ሆነ ለመምራት የምንጠቀምበት ዋነኛው መሣሪያችን ነው። እንደ ትራክት ባሉ ሌሎች ተስማሚ ጽሑፎች ተጠቅመን ጥናት ማስጀመር የምንችል ቢሆንም በተቻለ ፍጥነት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወደተባለው መጽሐፍ እንዲሸጋገሩ ለማድረግ መጣር ያስፈልገናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅሞ ጥናቶችን በማስጀመር ረገድ ግሩም ውጤቶች ተገኝተዋል።

ተማሪው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አጥንቶ ከጨረሰ በኋላ እድገት እያደረገ መሆኑን ካስተዋልን አምላክን አምልክ የተባለውን መጽሐፍ ማስጠናት እንችላለን። (ቈላ. 2:7) በገጽ 2 ላይ የሚገኘው የመጽሐፉ ዓላማ እንዲህ ይላል:- “መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክን የሚወዱ ሁሉ ውድ የሆኑትን እውነቶቹን ‘ከፍታና ጥልቀት እንዲገነዘቡ’ አጥብቆ ያበረታታል። (ኤፌሶን 3:18) ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ለዚሁ ዓላማ ነው። በመንፈሳዊ እንድታድግና አምላክ ወደሚያመጣው አዲስ ዓለም በሚመራው ጠባብ መንገድ ላይ ለመጓዝ በተሻለ ሁኔታ እንድትታጠቅ ይረዳሃል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።”

ተማሪው ሁለቱንም መጻሕፍት አጥንቶ ከመጨረሱ በፊት ብቃቶቹን አሟልቶ ቢጠመቅም እንኳ እነዚህን መጻሕፍት አጥንቶ መጨረስ ይኖርበታል። ተማሪው የተጠመቀ ቢሆንም አስጠኚው ሰዓት፣ ተመላልሶ መጠየቅና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሪፖርት ማድረግ ይችላል። በተጨማሪም በጥናቱ ላይ እንዲገኝ የተጋበዘ አስፋፊ ተሳትፎ እስካደረገ ድረስ ሰዓቱን መያዝ ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ