የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/08 ገጽ 4
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአረጋውያን መንከባከቢያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙትን አትርሷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ከቤተሰብና ከጉባኤ ርቀው ቢኖሩም አልተረሱም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • “መሞትሽ የማይቀር ነው!”
    ንቁ!—2000
  • የሐኪም ሙያ
    ንቁ!—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 4/08 ገጽ 4

የጥያቄ ሣጥን

◼ አንድ የይሖዋ ምሥክር በሃይማኖታዊ ድርጅት በሚተዳደር ሆስፒታል ውስጥ መታከሙ ወይም የመጦሪያ ተቋም ውስጥ መግባቱ ተገቢ ነው?

በርካታ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ወይም ሥር የሰደደ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች የሚንከባከቡ ሆስፒታሎች አሊያም የመጦሪያ ተቋማት አሏቸው። በጥቅሉ ሲታይ እነዚህ ተቋማት የታላቂቱ ባቢሎንን ዓላማ ለማራመድ ተብለው የተቋቋሙ አይደሉም። (ራእይ 18:2, 4) ተቋማቱ መጀመሪያ ላይ የተቋቋሙት ገቢ ለማስገኘት ታስበው ሊሆን ይችላል። በዛሬው ጊዜ፣ አንዳንድ ሆስፒታሎች በሃይማኖት ድርጅቶች ሥር እንደሆኑ ተደርገው የሚታሰቡት ቀድሞ በነበራቸው ስም ብቻ ሲሆን ሌሎቹ ግን አሁንም ድረስ በውስጣቸው የሚሠሩ ቀሳውስት አሏቸው።

አንድ የይሖዋ ምሥክር፣ ሆስፒታል አሊያም መጦሪያ ተቋም መግባት ሲያስፈልገው ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ግንኙነት ሊኖረው ወደሚችል ተቋም መሄድ ይገባው እንደሆነና እንዳልሆነ መወሰን ያለበት ራሱ ነው። አንድ ክርስቲያን ሕሊናው እንዲሄድ ሊፈቅድለት የሌላው ሕሊና ደግሞ እንደዚያ እንዳያደርግ ሊከለክለው ይችላል። (1 ጢሞ. 1:5) በአንድ ሰው ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ፤ እስቲ እነዚህ ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ እንመልከት።

ለምሳሌ ያህል፣ በአካባቢው የሚገኘው ሆስፒታል ወይም የመጦሪያ ተቋም በሃይማኖታዊ ድርጅት ስም የተቋቋመው ብቻ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ በአቅራቢያው የሚገኝ ሌላ ተቋም ቢኖርም የተሻለ አገልግሎት የሚሰጠው ግን ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚታሰበው ተቋም ሊሆን ይችላል። አንድን በሽታ ለማከም የሚያስችል ለየት ያለ መሣሪያ የሚገኘው አሊያም የሚመረምርህ ወይም ቀዶ ሕክምና የሚያደርግልህ ሐኪም ታካሚዎቹን የሚያስተናግደው በሃይማኖታዊ ድርጅት ስም በተቋቋመ ሆስፒታል ብቻ ሊሆን ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ፣ ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሆስፒታሎች ደምን በተመለከተ ያለህን ክርስቲያናዊ አመለካከት ሲያከብሩልህ ሌሎች የግል ወይም የመንግሥት ሆስፒታሎች ግን ውሳኔህን ላይቀበሉ ይችላሉ። በመሆኑም ወደ የትኛው ሆስፒታል መግባት እንዳለብህ በምትወስንበት ጊዜ እነዚህን ጉዳዮች ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብህ ይሆናል።

በገንዘብህ እንደምታገኘው አንድ ዓይነት አገልግሎት አድርገህ በማሰብ ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ግንኙነት ወዳለው አንድ ሆስፒታል ወይም የመጦሪያ ተቋም ለመግባት ትወስን ይሆናል። እንዲሁም የሃይማኖት ድርጅቱ አንድ ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ እያደረገ እንዳለና ተቋሙ በክፍያ ከሚሰጠው አገልግሎት መጠቀም የሐሰት ሃይማኖትን ለመደገፍ ከሚደረግ የፈቃደኝነት መዋጮ የተለየ እንደሆነ አድርገህ ትመለከተው ይሆናል። ይህ ደግሞ አንድን ዕቃ ከመግዛት ወይም ለተሰጠህ አገልግሎት ገንዘብ ከመክፈል ተለይቶ አይታይም።

እርግጥ ነው፣ ክርስቲያን እንደመሆንህ መጠን እንዲህ በመሰሉ ሁኔታዎች ውስጥ ስትሆን በማንኛውም ዓይነት የሐሰት አምልኮ እንቅስቃሴ ላለመካፈል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል። ከዚህም በተጨማሪ በተቋሙ የሚሠሩትን ወይም ተቋሙን ለመጎብኘት የሚመጡትን የሃይማኖት ሰዎች “አባ” ወይም “ሲስተር” እንደሚሉት ባሉ ሃይማኖታዊ የማዕረግ ስሞች መጥራት አይኖርብህም። (ማቴ. 23:9) ተቋሙ ሕክምና ወይም ሌላ ዓይነት አገልግሎት ከመስጠት ውጪ ሌላ ነገር እንደማይጠብቅብህ ማረጋገጥ ይኖርብሃል።

ሆስፒታል በምትገባበት ጊዜ የይሖዋ ምሥክር መሆንህንና የጉባኤህ ሽማግሌዎች እየመጡ እንዲጠይቁህ እንደምትፈልግ ልትነግራቸው ትችላለህ። ይህም በሆስፒታሉ በምትቆይበት ጊዜ ተገቢ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ እንድታገኝ ያስችልሃል።—1 ተሰ. 5:14

የይሖዋ ምሥክር የሆኑ የቤተሰብ አባላት፣ የጉባኤ ሽማግሌዎች እንዲሁም ሌሎች ወንድሞችና እህቶች በተለይ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች በሚያስተዳድሯቸው የመጦሪያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙትን አረጋውያን በመንፈሳዊ የመንከባከብ ኃላፊነት አለባቸው። በዚህ ረገድ ትጋት የተሞላበት ጥረት ማድረጋችን ለእነዚህ አረጋውያን ትልቅ ማበረታቻ የሚሆንላቸው ከመሆኑም በላይ በተቋሙ ውስጥ በሚካሄዱት ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች፣ ክብረ በዓሎች ወይም ሌሎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ሳያውቁ እንዳይካፈሉ ይጠብቃቸዋል።

እያንዳንዱ ግለሰብ እነዚህን ነጥቦች በአእምሮው ይዞ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ በማጤን የትኛው ሆስፒታል ወይም የመጦሪያ ተቋም ውስጥ መግባት እንዳለበት የራሱን ውሳኔ ማድረግ ይኖርበታል።—ገላ. 6:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ