መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ብዙ ሰዎች፣ አምላክ አፍቃሪ ነው ብለው ቢያምኑም ሰዎችን ለዘላለም እንደሚያሠቃይ የሚናገረው ትምህርት ግራ ያጋባቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ክፉ ወይም ቂመኛ እንዳልሆነ ያስተምራል። [ሕዝቅኤል 18:23ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትኩረት የሚስቡ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ይዟል።”
ንቁ! ኅዳር 2008
“በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አምላክ ይጸልያሉ። እኛም እንዲህ እንድናደርግ ግብዣ ቀርቦልናል። [1 ጴጥሮስ 5:7ን አንብብ።] ሆኖም በሕይወት ውስጥ በሚያጋጥሙት ጫናዎች የተነሳ ቅን የሆኑ በርካታ ሰዎች እንኳ ጸሎታቸው አጭርና በዘልማድ የሚቀርብ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በመሆኑም እያንዳንዳችን ‘የጸሎቴን ይዘት ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?’ የሚለውን ጥያቄ ማንሳታችን አስፈላጊ ነው። [ገጽ 26ን አሳየው።] ይህ ርዕስ፣ የአምልኮታችን ዋነኛ ክፍል ከሆነው ከጸሎት ጋር በተያያዘ ልናሻሽላቸው የምንችላቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“በዚህ ወቅት ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ያስባሉ። ኢየሱስ በሕይወትዎ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ፈለግ እንድንከተል ያበረታታናል። [1 ጴጥሮስ 2:21ን አንብብ።] እንዲህ ማድረጋችን ደግሞ ደስተኛና ጥሩ ሰዎች እንድንሆን ያስችለናል። ይህ መጽሔት የዚህን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2008
“ሰዎች ይህን ጥያቄ ለዘመናት ሲጠይቁ ኖረዋል። [በሽፋኑ ላይ ያለውን ጥያቄ አሳየው።] ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መልሱን ለማግኘት ወደ አምላክ ዞር ማለት ያለብን ለምን እንደሆነ ልብ ይበሉ። [መዝሙር 100:3ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚል ይህ መጽሔት ያብራራል።”