መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በተሳሳተ ሃይማኖታዊ ቅንዓት ተገፋፍተው መጥፎ ነገሮችን ይሠራሉ። የሚታለሉት ለምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንድናደርግ እንደሚያበረታታን ልብ ይበሉ። [1 ዮሐንስ 4:1ን አንብብ።] ይህ ርዕስ የምናምንባቸውን ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማወዳደር ያለብን ለምን እንደሆነ ያብራራል።” ገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! መስከረም 2010
ማቴዎስ 5:39ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “እዚህ ላይ ኢየሱስ ግፍ ሲፈጸምብን ዝም ብለን መጎዳት አለብን ብሎ እየተናገረ ያለ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ ራስን ስለ መከላከልና ሕጋዊ ከለላ ለማግኘት እርምጃ ስለ መውሰድ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ያብራራል።” ገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተለያየ ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች ይጸልያሉ። አምላክ ጸሎትን እንደሚሰማና ምላሽ እንደሚሰጥ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ እንድንጸልይ ያበረታታናል። [ፊልጵስዩስ 4:6, 7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጸሎትን በተመለከተ ብዙ ጊዜ ለሚነሱ ሰባት ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።”
ንቁ! ጥቅምት 2010
“ሰዎች በትዳር ጓደኛቸው፣ በፖለቲከኞችና በሌሎች እንደሚጭበረበሩ ብዙ ጊዜ እንሰማለን። እምነት የሚጣልበት ሰው ማግኘት ከባድ እየሆነ እንደመጣ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በርካታ ሰዎች ይህ ጥቅስ እየተፈጸመ እንደሆነ ይሰማቸዋል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1-5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አሁንም ቢሆን እምነት የሚጣልባቸው ሰዎችን የት ማግኘት እንደምንችል ይገልጻል።”