መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“መላእክት እኛ የምናደርጋቸው ነገሮች የሚያሳስቧቸው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚል ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ይዟል። [ሉቃስ 15:10ን አንብብ።] ይህ ርዕስ መንፈሳዊ ፍጥረታት ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን ስለሚችሉበት መንገድ ኢየሱስ የተናገረውን ሐሳብ ያብራራል።” ገጽ 16 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ኅዳር 2010
ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማንኛውንም ነገር ማመን እንዳለብን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥንቷ ግብጽ የሚናገረው ነገር ትክክል እንደሆነ የአርኪኦሎጂ ግኝቶችና የዓለም ታሪክ ያረጋገጡት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” ገጽ 15 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ብዙ ሰዎች በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ የማሰብ ችሎታ ያላቸው አካላት እንዳሉና በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ያምናሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ራእይ 12:7-9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ የሚኖሩ አካላት ሊረዱን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት እንደሆነና ከእነሱ ጋር ግንኙነት መፍጠር ተገቢ መሆን አለመሆኑን ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2010
“መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን የማይናገር ቢሆንም የገና በዓል ታኅሣሥ 25 የሚከበረው ለምን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጥቅስ እንደሚጠቁመው ኢየሱስ የተወለደው በክረምት ወቅት ሊሆን አይችልም። [ሉቃስ 2:8ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንዳንድ የተለመዱ የገና በዓል ልማዶች ምንጭ ምን እንደሆነ ይጠቁማል።”