የቤቱ ባለቤት ነጥቡን ራሱ እንዲያመዛዝን መርዳት
1. በአገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ የሆነው የትኛው አቀራረብ ነው?
1 በአገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ የሆነው የትኛው አቀራረብ ነው? ድርቅ ያለ አመለካከት መያዝ ወይስ የምናነጋግረው ሰው የማመዛዘን ችሎታውን ተጠቅሞ ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ መርዳት? ሐዋርያው ጳውሎስ በተሰሎንቄ የሚገኙ አይሁዳውያንን ሲያነጋግራቸው የማመዛዘን ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ አጋጣሚ ሰጥቷቸው ነበር፤ “ከዚህም የተነሳ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ አማኞች” ሆነዋል። (ሥራ 17:2-4) የምናነጋግራቸው ሰዎች የማመዛዘን ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
2. ምሥራቹን በምንሰብክበት ጊዜ የጳውሎስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
2 ስሜታቸውንና አመለካከታቸውን ግምት ውስጥ አስገቡ፦ በክልላችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ነጥቡን እንዲያመዛዝኑ መርዳት ከፈለግን ስሜታቸውን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል። ጳውሎስ፣ በአርዮስፋጎስ ለማያምኑ ግሪኮች ንግግር መስጠት ሲጀምር የሚያውቁትንና የሚያምኑበትን ነገር ጠቅሷል። (ሥራ 17:22-31) እንግዲያው መግቢያ ስትዘጋጁ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያምኑባቸውን እንዲሁም የሚያበሳጯቸውን ነገሮች ልብ በሉ። (1 ቆሮ. 9:19-22) የምታነጋግሩት ሰው ተቃውሞ ካነሳ በጋራ የምትስማሙባቸውን ነጥቦች ፈልጋችሁ በዚያ ላይ ለመወያየት ጥረት አድርጉ።
3. ጥያቄዎችን ጥሩ አድርገን በመጠቀም የምናነጋግራቸው ሰዎች እንዲያመዛዝኑ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
3 ጥያቄዎችን ጥሩ አድርጋችሁ ተጠቀሙ፦ አንድ መንገደኛ ያለበትን ቦታ እስካላወቅን ድረስ የሚሄድበትን አካባቢ በተመለከተ አቅጣጫ ልንጠቁመው አንችልም። በተመሳሳይም የቤቱን ባለቤት አመለካከት ካላወቅን ወደ ትክክለኛው መደምደሚያ እንዲደርስ መርዳት አንችልም። ኢየሱስ የሚያነጋግራቸውን ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ ማስረዳት ከመጀመሩ በፊት አመለካከታቸውን ለማወቅ ብዙ ጊዜ ጥያቄዎችን ይጠይቃቸው ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ሰው ኢየሱስን “የዘላለም ሕይወት የማገኘው ምን ባደርግ ነው?” ብሎ በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስ መልስ ከመስጠቱ በፊት የግለሰቡን አመለካከት ለመረዳት ጥሯል። (ሉቃስ 10:25-28) በሌላ ጊዜ ደግሞ ጴጥሮስ የተሳሳተ መልስ በሰጠበት ጊዜ ኢየሱስ የጴጥሮስን አመለካከት ለማስተካከል ጥያቄዎችን ጥሩ አድርጎ ተጠቅሟል። (ማቴ. 17:24-26) እንግዲያው የምናነጋግረው ሰው ጥያቄ ከጠየቀን ወይም የተሳሳተ መልስ ከሰጠን በጉዳዩ ላይ እንዲያመዛዝን ለመርዳት ጥያቄዎችን መጠቀም እንችላለን።
4. የምናነጋግረው ሰው እንዲያመዛዝን ለመርዳት ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
4 የምናነጋግረው ሰው እንዲያመዛዝን ስንረዳው ታላቅ አስተማሪ የሆነውን የኢየሱስን እንዲሁም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ሌሎች ውጤታማ ወንጌላውያንን ምሳሌ እንከተላለን። እንዲህ በማድረግ ለምናነጋግረው ሰው አክብሮት እንዳለን እናሳያለን። (1 ጴጥ. 3:15) በዚህም ምክንያት ግለሰቡ ተመልሰን እንድናነጋግረው ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል።