የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/12 ገጽ 1
  • ‘ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተበሳጨ የቤት ባለቤት መልስ መስጠት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ደፋር ግን ሰላማውያን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • የቤቱ ባለቤት ነጥቡን ራሱ እንዲያመዛዝን መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • በአገልግሎታችሁ ወርቃማውን ሕግ ተግባራዊ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 12/12 ገጽ 1

‘ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ’

1. የምናነጋግረው ሰው ቢበሳጭ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል?

1 የይሖዋ ሕዝቦች ሰላም ወዳድ ናቸው፤ ለሰዎች የምንሰብከውም የሰላም መልእክት ነው። (ኢሳ. 52:7) ያም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በራቸውን ስናኳኳ ይበሳጫሉ። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመን ሰላማዊ ለመሆን ምን ሊረዳን ይችላል?—ሮም 12:18

2. አስተዋዮች መሆናችን አስፈላጊ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

2 አስተዋዮች ሁኑ፦ አንዳንድ ሰዎች በቁጣ የሚገነፍሉት እውነትን ስለሚቃወሙ ይሆናል፤ ሌሎች ግን የሚበሳጩት በመልእክቱ ላይሆን ይችላል። ምናልባትም መጥፎ ጊዜ ላይ ሄደን ይሆናል። አሊያም የቤቱ ባለቤት ባጋጠመው አንድ ችግር ምክንያት ተበሳጭቶ ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው የተበሳጨው በምሥራቹ ቢሆንም እንኳ ግለሰቡ እንዲህ የተሰማው ስለተታለለ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል። (2 ቆሮ. 4:4) እንግዲያው አስተዋዮች መሆናችን እንድንረጋጋና የቤቱን ባለቤት በግለሰብ ደረጃ እንዳላበሳጨነው እንድናስታውስ ያደርገናል።—ምሳሌ 19:11

3. ለቤቱ ባለቤት አክብሮት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

3 አክብሮት አሳዩ፦ በክልላችን ያሉ ብዙ ሰዎች በጥብቅ የሚከተሏቸው እምነቶች አሏቸው። (2 ቆሮ. 10:4) እንዲሁም መልእክቱን የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብት አላቸው። ግለሰቡ የሚያምንባቸውን ነገሮች ማቃለል ወይም ከእሱ እንደምንበልጥ እንደሚሰማን የሚያሳይ ነገር ማድረግ የለብንም። ቤቱን ለቅቀን እንድንሄድ ቢነገረን በአክብሮት መታዘዝ ይኖርብናል።

4. ለዛ ባለው መንገድ መናገር ሲባል ምን ማለት ነው?

4 አነጋገራችሁ ለዛ ያለው ይሁን፦ ሰዎች መጥፎ ነገር ቢናገሩንም እንኳ ተረጋግተን ለዛ ባለው መንገድ መልስ መስጠት ይኖርብናል። (ቆላ. 4:6፤ 1 ጴጥ. 2: 23) ወደ ክርክር ከመሄድ ይልቅ ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ለማንሳት ሞክሩ። ምናልባትም የቤቱ ባለቤት የተቃወመበትን ምክንያት በደግነት ልንጠይቀው እንችላለን። አብዛኛውን ጊዜ ግን ግለሰቡን እንዳናበሳጨው ውይይቱን ብናቋርጥ የተሻለ ነው።—ምሳሌ 9:7፤ 17:14

5. በአገልግሎት ሰላማዊ መሆናችን ምን ጥቅሞች ያስገኝልናል?

5 ሰላማዊ ከሆንን የቤቱ ባለቤት የሰጠነውን ምላሽ ሊያስታውስና ሌላ ሰው ሲመሠክርለት ለማዳመጥ ሊነሳሳ ይችላል። (ሮም 12:20, 21) ግለሰቡ በተቃውሞው ቢገፋበት እንኳ አንድ ቀን ወንድማችን ሊሆን ይችላል። (ገላ. 1:13, 14) የምናነጋግረው ሰው ለእውነት ፍላጎት ባይኖረውም፣ ራሳችንን የምንገዛና ሰላማዊ ከሆንን ይሖዋን እናስከብራለን፤ እንዲሁም የምናስተምረውን ትምህርት እናስውባለን።—2 ቆሮ. 6:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ