በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተበሳጨ የቤት ባለቤት መልስ መስጠት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸው አብዛኞቹ ሰዎች ሰው አክባሪ ናቸው። ሆኖም ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው አንዳንድ ሰዎች ይጠሉናል። (ዮሐ. 17:14) በመሆኑም አንድ ሰው ስናነጋግረው ቢበሳጭ አያስገርመንም። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመን ይህን ተልእኮ የሰጠንን ይሖዋን በሚያስደስት መንገድ መልስ መስጠት እንፈልጋለን። (ሮም 12:17-21፤ 1 ጴጥ. 3:15) እንዲህ ማድረጋችን ሁኔታው እንዳይባባስ ሊያደርግ ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ለቤቱ ባለቤትም ሆነ ሁኔታውን ለሚመለከቱ ሌሎች ሰዎች ጥሩ ምሥክርነት የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር የይሖዋ ምሥክሮች ሌላ ጊዜ መጥተው ሲያነጋግሯቸው ጥሩ ምላሽ እንዲሰጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።—2 ቆሮ. 6:3
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
ይህን ማድረግ የምትችሉት እንዴት እንደሆነ በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ወቅት ተለማመዱ።
ከተበሳጨው ግለሰብ ጋር ከተለያያችሁ በኋላ ከዚህ የተሻለ ምን መልስ መስጠት ትችሉ እንደነበር ከአገልግሎት ጓደኛችሁ ጋር ተወያዩ።