የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/94 ገጽ 2
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውይይት የሚያስቆሙ ሐሳቦች ሲሰነዘሩ መልስ መስጠት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የቤቱ ባለቤት ነጥቡን ራሱ እንዲያመዛዝን መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • አቀላልና ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቆችን ማድረግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ሕይወት አድን በሆነው አገልግሎታችን ስኬታማ በሆነ መንገድ መካፈል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 6/94 ገጽ 2

የጥያቄ ሣጥን

◼ አንድ ሰው የይሖዋ ምሥክሮች ቤቱ መጥተው እንዲያነጋግሩት የማይፈልግ መሆኑን አምርሮ ቢናገር ምን መደረግ አለበት?

ሃይማኖት ነክ ጉዳዮችን ለማወያየት የሚፈልጉ ሰዎች በተለይ ደግሞ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቱ እንዲመጡ የማይፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ምልክት እቤቱ በር ላይ በምናይበት ጊዜ የሰውዬውን ፍላጎት በማክበር ከማንኳኳት ብንቆጠብ የተሻለ ይሆናል።

አንዳንድ ጊዜ ዕቃ ሻጮችን ወይም እየዞሩ የርዳታ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ቤታቸው እንዲመጡ የማይፈልጉ መሆናቸውን የሚገልጽ ምልክት እናይ ይሆናል። የምንሠራው ሥራ በበጎ ፈቃደኝነት የሚደረግ ሃይማኖታዊ ሥራ በመሆኑ ይህ እኛን አይመለከትም። እንዲህ ያለው ምልክት ያለባቸውን በሮች ማንኳኳት ተገቢ ይሆናል። የቤቱ ባለቤት ተቃውሞ ቢያሳይ እነዚህ ምልክቶች እኛን የማይመለከቱን የመሰለን ለምን እንደሆነ በዘዴ ልናስረዳው እንችላለን። የቤቱ ባለቤት የከለከለው የይሖዋ ምሥክሮችን ጭምር መሆኑን ግልጽ ካደረገ ፍላጎቱን እናከብርለታለን።

በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ስንሠራ የቤቱ ባለቤት ተበሳጭቶ ሁለተኛ ቤቴ እንዳትመጡ በማለት አምርሮ በግልጽ ይናገር ይሆናል። ጉዳዩን በምክንያት ለመወያየት ፈቃደኛ ካልሆነ ውሳኔውን እናከብርለታለን። ለወደፊት በአገልግሎት ክልሉ የሚሠሩ አስፋፊዎች ያን ቤት እንዳያንኳኩ ቀኑ የተጻፈበት ማስታወሻ ከአገልግሎት ክልሉ ካርድ ጋር ተያይዞ መቀመጥ ይኖርበታል።

እነዚህን ቤቶች እስከመጨረሻው አናኳኳቸውም ማለት አይደለም። አግኝተናቸው የነበሩት ሰዎች ለቀው ሄደው ይሆናል። መልእክቱን የሚቀበል ሌላ የቤተሰቡ አባል ይኖር ይሆናል። በተጨማሪም አነጋግረነው የነበረው ሰው የሐሳብ ለውጥ አድርጎ ሊሆን ስለሚችል ሄደን ብናነጋግረው ደስ ይለው ይሆናል። ስለዚህ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የዚያ ቤት ነዋሪዎች በአሁኑ ጊዜ ያላቸውን ስሜት ለማወቅ በዘዴ መጠየቅ ይገባል።

ከላይ የተጠቀሰው ችግር ያለባቸው ጉባኤዎች ባይንኳኩ የተሻለ እንደሚሆን ሐሳብ የተሰጠባቸውን ቤቶች እየመዘገቡ የአገልግሎት ክልሉን መዝገብ በዓመት አንድ ጊዜ እንደገና መመርመር ይኖርባቸዋል። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ዘዴና ልምድ ያላቸው አንዳንድ አስፋፊዎች እነዚህን ቤቶች እንዲያንኳኩ ሊመደቡ ይችላሉ። በዚህ ቤት ይኖር የነበረው ሰው አሁንም መኖር አለመኖሩን ለመጠየቅ የሄድን መሆናችንን ልንናገር እንችላለን። አስፋፊው ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 15–24 ላይ “ውይይት ለማስቆም ለሚሰነዘሩ ሐሳቦች ምን መልስ መስጠት ይቻላል?” በሚለው ርዕስ ሥር የቀረቡትን ልዩ ልዩ ማስረጃዎች በደንብ የሚያውቅ መሆን ይኖርበታል። በመጠኑም ቢሆን ደህና ምላሽ ከሰጠ ለወደፊት የሚደረጉት ተመላልሶ መጠየቆች በወትሮው መንገድ ሊደረጉ ይችላሉ። የቤቱ ባለቤት በተቃውሞው ከቀጠለ ግን እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ወደ ቤቱ መሄድ አይኖርብንም። የጉባኤው የሽማግሌዎች አካል ሁኔታው ለየት ባለ መንገድ መያዝ የሚያስፈልገው ጉዳይ መሆን አለመሆኑን ሊወሰን ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ