ሕጋዊ ድረ ገጻችን—ለቤተሰብና ለግል ጥናት ተጠቀሙበት
በቅርቡ የወጡ መጽሔቶችን ኢንተርኔት ላይ አንብቡ፦ በወረቀት የታተሙት መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ጉባኤያችን ከመድረሳቸው ከበርካታ ሳምንታት በፊት ኢንተርኔት ላይ ልናነባቸው እንችላለን። በተጨማሪም በድምፅ የተቀዳውን የእነዚህን መጽሔቶች ንባብ ከኢንተርኔት ላይ በማውረድ ማዳመጥ ይቻላል።—መጀመሪያ “የሕትመት ውጤቶች” ከዚያም “መጽሔቶች” የሚለውን ተጫን፤ በድምፅ የተቀዳውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማግኘት ይቻላል።
በድረ ገጹ ላይ ብቻ የሚወጡ ርዕሶችን አንብቡ፦ “ለታዳጊ ወጣቶች፣” “መጽሐፍ ቅዱስን መማሪያዬ፣” “ቤተሰብ የሚወያይበት” እና “የወጣቶች ጥያቄ” የመሳሰሉት አንዳንድ ዓምዶች ከዚህ በኋላ የሚወጡት በድረ ገጻችን ላይ ብቻ ይሆናል። ከኢንተርኔት ላይ የሚገኙትን እነዚህን ርዕሶች በግል ወይም በቤተሰብ ጥናታችሁ ወቅት ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ።—“ባይብል ቲቺንግስ” በሚለው ሥር “ችልድረን” ወይም “ቲንኤጀርስ” (እንግሊዝኛ) የሚለውን ተጫን።
ወቅታዊ ዜናዎችን ተመልከቱ፦ በዓለም ዙሪያ ስለምናከናውነው ሥራ የሚገልጹ አበረታች ሪፖርቶችንና ተሞክሮዎችን ማንበብ እንዲሁም የቪዲዮ ክሊፖችን መመልከት ትችላላችሁ። ስለ ተፈጥሮ አደጋዎችና በወንድሞቻችን ላይ ስለደረሰው ስደት የሚገልጹት ሪፖርቶች፣ በወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ለይተን በመጥቀስ እንድንጸልይ ይረዱናል። (ያዕ. 5:16)—“ኒውስ” (እንግሊዝኛ) የሚለውን ተጫን።
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍትን ተጠቅማችሁ ምርምር አድርጉ፦ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት በቋንቋችሁ የሚገኝ ከሆነ በኮምፒውተር አሊያም በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች አማካኝነት የዕለት ጥቅስ ኢንተርኔት ላይ እንዳላችሁ ማንበብ ወይም በቅርብ በወጡ አንዳንድ ጽሑፎቻችን ላይ ምርምር ማድረግ ትችላላችሁ። —መጀመሪያ “የሕትመት ውጤቶች” ከዚያም “የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት” የሚለውን ተጫን፤ ወይም በኢንተርኔት ማሰሻህ ላይ www.wol.jw.org የሚለውን አድራሻ ጻፍ።
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)
ሞክሩት
1 ሥዕሉን ወይም “ዳውንሎድ” የሚለውን ጠቅ አድርግ። በዚህ ጊዜ ሥዕሉ በፒዲኤፍ ፋይል ይከፈታል። ሥዕሉን ካተምክ በኋላ ልጆችህን ለማስተማር ተጠቀምበት።
2 ቪዲዮዎችን ለመመልከት የማጫወቻ ምልክቱን ተጫን።