ሕጋዊ ድረ ገጻችን—ለአገልግሎት ተጠቀሙበት
ሰዎች ድረ ገጹን እንዲመለከቱ ጠቁሟቸው፦ ከእኛ ጋር ለመወያየት ወይም ጽሑፎችን ለመቀበል የሚያቅማሙ ሰዎች ቤታቸው ውስጥ ብቻቸውን ሲሆኑ jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን በመቃኘት ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ለማወቅ ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ። እንግዲያው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድረ ገጹን ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጉ።
ጥያቄዎችን ለመመለስ፦ አንዳንድ ጊዜ በአገልግሎት የምናገኛቸው፣ ፍላጎት ያላቸው ወይም የምናውቃቸው ሰዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ወይም ስለምናምንባቸው ነገሮች ጥያቄ ያነሱ ይሆናል። እንደ ሞባይል ስልክ ባለ ኢንተርኔት ለመጠቀም በሚያስችል ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ወይም በኮምፒውተር ተጠቅማችሁ እዚያው ባላችሁበት የጥያቄውን መልስ አሳዩአቸው። የተጠቀሱትን ጥቅሶች ቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማንበቡ በአብዛኛው ተመራጭ ነው። ኢንተርኔት ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ግለሰቡ jw.org የተባለውን ድረ ገጽ ተጠቅሞ መልሱን ራሱ እንዴት ማግኘት እንደሚችል ግለጹለት።—“ባይብል ቲቺንግስ” በሚለው ሥር “ባይብል ኩዌስችንስ አንሰርድ” (እንግሊዝኛ) የሚለውን ወይም “ስለ እኛ” በሚለው ሥር “ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች” የሚለውን ተጫን።
አንድ ርዕስ ወይም ጽሑፍ ለምታውቀው ሰው ላክ፦ ከኢንተርኔት ላይ ያወረዳችሁትን የፒዲኤፍ ወይም የኢፐብ ፋይል ኢ-ሜይላችሁ ላይ አባሪ አድርጋችሁ መላክ ትችላላችሁ። ወይም ደግሞ በድምፅ የተቀረጸውን የጽሑፉን ንባብ ከኢንተርኔት ላይ አውርደህ በሲዲ ልትገለብጠው ትችላለህ። ሙሉ መጽሐፍ፣ ብሮሹር ወይም መጽሔት በሲዲም ሆነ በኢ-ሜይል ተጠቅመህ ላልተጠመቀ ሰው በሰጠህ ቁጥር ጽሑፉን እንዳበረከት በማሰብ ልትቆጥር ትችላለህ። ጽሑፎችን ለማታውቁት ሰው ወይም በገፍ መላክ አይኖርባችሁም። በተጨማሪም ከድረ ገጻችን ላይ የምታወርዱትን ነገር በማንኛውም ሌላ ድረ ገጽ ላይ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም።—“የሕትመት ውጤቶች” የሚለውን ተጫን።
ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ወቅታዊ ዜናዎችን ለማሳየት፦ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ወይም ለሌሎች ሰዎች ወቅታዊ ዜናዎችን በማሳየት በዓለም ዙሪያ ለሚሠራው ሥራችን ወይም ለክርስቲያናዊ አንድነታችን አድናቆት እንዲኖራቸው ማድረግ እንችላለን። (መዝ. 133:1)—“ኒውስ” (እንግሊዝኛ) የሚለውን ተጫን።
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ]
(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)
ሞክሩት
1 መጀመሪያ “የሕትመት ውጤቶች” የሚለውን ተጫን። በዚህ ጊዜ የጽሑፎች ዝርዝር ይወጣል። ከዚያም በጽሑፍ የተዘጋጀውን ለማውረድ ከወረቀት ምልክቱ አጠገብ ያሉትን ቁልፎች ተጫን፤ በድምፅ የተቀዳውን ለማውረድ ደግሞ ከማዳመጫው ምልክት አጠገብ ያሉትን ቁልፎች ተጫን።
2 በጽሑፉ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን ርዕሶች እንዲያወጣልህ MP3 የሚለውን ተጫን። ከዚያም የምትፈልገውን ርዕስ በመጫን ማውረድ አሊያም ▸ በመንካት ማዳመጥ ትችላለህ።
3 ጽሑፉን በሌላ ቋንቋ ማውረድ ከፈለግክ ከመምረጫው ውስጥ የምትፈልገውን ቋንቋ መምረጥ ትችላለህ።