ሕጋዊ ድረ ገጻችን—ከእናንተ የተለየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን ለመርዳት ተጠቀሙበት
ድረ ገጹን አሳዩት፦ ለምታነጋግሩት ሰው “የድረ ገጹ ቋንቋ” የሚለውን ተጠቅሞ ገጹን በራሱ ቋንቋ ማየት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳዩት። (በአንዳንድ ቋንቋዎች የሚታየው የድረ ገጹ የተወሰነው ክፍል ብቻ ነው።)
በራሱ ቋንቋ የተዘጋጀ ጽሑፍ አሳዩት፦ ከጽሑፎቻችን መካከል አንዱን ለምሳሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ወይም እውነቱን ማወቅ የተባለውን ትራክት ለምታናግሩት ሰው አሳዩት። ግለሰቡ የሚናገረውን ቋንቋ “አንብብ በ” ከሚለው አጠገብ ካለው ሣጥን ውስጥ መምረጥ ትችላላችሁ።
የተቀዳውን ጽሑፍ እንዲያዳምጥ አድርጉት፦ ግለሰቡ በሚናገረው ቋንቋ በድምፅ የተቀዳ ርዕስ ካለ አጫውቱለት። ሌላ ቋንቋ እየተማርክ ከሆነ በዚያ ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎችን ስታነብብ በድምፅ የተቀዳውንም አብረህ በማዳመጥ የቋንቋ ችሎታህን ማሻሻል ትችላለህ።—“የሕትመት ውጤቶች” በሚለው ሥር “መጻሕፍትና ብሮሹሮች” ወይም “መጽሔቶች” የሚለውን ተጫን፤ በድምፅ የተቀዳውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማግኘት ይቻላል።
መስማት ለተሳናቸው መመሥከር፦ መስማት የተሳነው ሰው ካጋጠማችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከመጽሐፍ፣ ከብሮሹር ወይም ከትራክት ላይ የተወሰደን አንድ ክፍል በምልክት ቋንቋ ቪዲዮ አሳዩት።—መጀመሪያ “የሕትመት ውጤቶች” ከዚያም “ምልክት ቋንቋ” የሚለውን ተጫን።
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ]
(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)
ሞክሩት
1 የመረጥከውን ርዕስ (በቋንቋህ የተዘጋጀ ከሆነ) ለማጫወት ▸ ተጫን ወይም “የማውረጃ አማራጮች” በሚለው ሥር ካሉት አማራጮች አንዱን ተጠቅመህ ጽሑፉን ማውረድ ትችላለህ።
2 “አንብብ በ” ከሚለው አጠገብ ካለው ሣጥን ውስጥ ሌላ ቋንቋ መርጠህ ጽሑፉን በዚያ ቋንቋ ማየት ትችላለህ።
3 ወደ ሌላ ርዕስ ወይም ምዕራፍ ለመሄድ “ቀጥል” የሚለውን ወይም “የርዕስ ማውጫ” ሥር ያሉትን ርዕሶች ተጫን።