ቪዲዮዎችን ለማስተማር ተጠቀሙባቸው
ይሖዋ ለአብርሃምና ለኤርምያስ አስፈላጊ የሆነ መረጃ ሲያስተላልፍላቸው መልእክቱን በቃል ከመናገር ባለፈ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅሟል። (ዘፍ. 15:5፤ ኤር. 18:1-6) እኛም ጥናቶቻችን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዲረዱና ከዚያም ጥቅም እንዲያገኙ ለመርዳት እንደ ቪዲዮ ባሉ የሚታዩ ነገሮች መጠቀም እንችላለን። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች አንዳንዶቹን ቪዲዮዎች መቼ ለጥናቶቻችን ማሳየት እንደምንችል ይጠቁማሉ። የእያንዳንዱ ተማሪ ሁኔታ የተለያየ ስለሚሆን እነዚህ ሐሳቦች እንደ ሕግ የቀረቡ እንዳልሆኑ መገንዘብ ይኖርባችኋል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ
◻ ምዕራፍ 1፣ ከአንቀጽ 17 በኋላ፦ አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉa የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 2፣ መጨረሻ ላይ፦ መጽሐፍ ቅዱስ—የሰው ልጅ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ለዘመናችን የሚሠራ መጽሐፍ የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 9፣ ከአንቀጽ 14 በኋላ፦ የይሖዋ ምሥክሮች—ምሥራቹን ለማወጅ የተደራጀ ሕዝብ የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 14፣ መጨረሻ ላይ፦ መጽሐፍ ቅዱስ—በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 15፣ ከአንቀጽ 10 በኋላ፦ መላው የወንድማማች ማኅበር የሚለውን ተመልከቱ
‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለው መጽሐፍ
◻ ምዕራፍ 3፣ ከአንቀጽ 15 በኋላ፦ የወጣቶች ጥያቄ—እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 4፣ መጨረሻ ላይ፦ የይሖዋን ሥልጣን አክብሩ የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 7፣ ከአንቀጽ 12 በኋላ፦ ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 9፣ ከአንቀጽ 6 በኋላ፦ ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች የሚለውን ተመልከቱ
◻ ምዕራፍ 17፣ መጨረሻ ላይ፦ ‘በእምነት እንጂ በማየት አትመላለሱ’ የሚለውን ተመልከቱ
ጥናቶቻችሁ ቢያዩዋቸው ሊጠቅሟቸው የሚችሉ ሌሎች ቪዲዮዎች አሉ? አዎ፣ ለምሳሌ ተቃውሞ እየደረሰባቸው ያሉ ግለሰቦች በሶቪየት ኅብረት ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በፈተና ወቅት ያሳዩት ጽናት ወይም የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተቋቁመዋል የተባሉትን ቪዲዮዎች በመመልከት ሊበረታቱ ይችላሉ። ወጣቶች ደግሞ አምላክን የሚያስከብር ግብ ላይ ለመድረስ ተጣጣሩ እና የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? ከሚሉት ቪዲዮዎች ጥቅም ማግኘት ይችላሉ። ከጥናቶቻችሁ ጋር ቪዲዮዎቹን መቼ መመልከት አሊያም ለእነሱ ማዋስ እንደምትችሉ ለማስታወስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እና ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ በተባሉት መጻሕፍት የግል ቅጂዎቻችሁ ላይ ምልክት አድርጉ። አዳዲስ ቪዲዮዎች ሲወጡ ደግሞ የጥናቶቻችሁን ልብ ለመንካት እንዴት ልትጠቀሙባቸው እንደምትችሉ አስቡ።—ሉቃስ 24:32
[የግርጌ ማስታወሻ]
a ቪዲዮዎቹን በእንግሊዝኛ ማግኘት ይቻላል።