አዲስ የምርምር መሣሪያ
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አስፋፊዎች ምርምር ለማድረግ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይሁንና መጽሐፉ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በዝርዝር የያዘ ስለሆነ የሚገኘው በተወሰኑ ቋንቋዎች ነው። በመሆኑም የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች የተባለው መጽሐፍ 170 ገደማ በሚሆኑ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለማመሳከሪያነት የተጠቀሱት በዋነኝነት ከ2000 በኋላ የወጡት ጽሑፎች ናቸው። ከዚህ በፊት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ በሚዘጋጅባቸው ቋንቋዎች የምርምር መርጃ መሣሪያ የተባለው መጽሐፍ በወረቀት ታትሞ አልወጣም፤ ከዚህ ይልቅ በዎችታወር ላይብረሪ እና በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ተካትቷል። የምርምር መርጃ መሣሪያው ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችህ መልስ ለማግኘት፣ ስላሳሰቡህ ጉዳዮች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ለጉባኤ ስብሰባዎችና ለቤተሰብ አምልኮ ለመዘጋጀት ይረዳሃል።