በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ እንዴት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እንደሚቻል ማሳየት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ብዙ ሰዎች በነፃ መጽሐፍ ቅዱስን እናስጠናለን ስንላቸው ምን ማለት እንደፈለግን ላይገባቸው ይችላል። ከሌሎች ሰዎች ጋር በቡድን እንዲማሩ ወይም የተልእኮ ትምህርት እንዲከታተሉ የምንጠይቃቸው ሊመስላቸው ይችላል። በመሆኑም እንዲያጠኑ በመጋበዝ ብቻ ከመወሰን ይልቅ እንዴት ማጥናት እንደሚችሉ ለምን አታሳዩአቸውም? በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ምናልባትም ደጃፋቸው ላይ እንደቆማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ቀላልና እውቀት የሚያስጨብጥ መሆኑን ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
ይሖዋ ጥናት ለማስጀመር የምታደርጉትን ጥረት እንዲባርክላችሁ በጸሎት ጠይቁት።—ፊልጵ. 2:13
አገልግሎት ስትወጡ ቢያንስ አንድ ጊዜ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ እንዴት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እንደሚቻል ለማሳየት ወይም መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ ለማሳየት ጥረት አድርጉ።