ለመታሰቢያው በዓል እየተዘጋጃችሁ ነው?
ኒሳን 13 ቀን 33 ዓ.ም. ነው። ኢየሱስ፣ ከመገደሉ በፊት ከቅርብ ወዳጆቹ ጋር የሚያሳልፈው የመጨረሻ ምሽት ይህ እንደሆነ ያውቃል። ከእነሱ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የፋሲካ በዓልን ካከበረ በኋላ የጌታ ራት የተባለ አዲስ በዓል ያቋቁማል። እንዲህ ያለው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል፣ ዝግጅት እንደሚጠይቅ እሙን ነው። በመሆኑም ለበዓሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። (ሉቃስ 22:7-13) ከዚያ ጊዜ አንስቶ፣ የመታሰቢያውን በዓል ማክበር የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ለዚህ ዓመታዊ በዓል ዝግጅት ያደርጋሉ። (ሉቃስ 22:19) ታዲያ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. (ሚያዝያ 3 ቀን 2015) ለሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ምን ዓይነት ዝግጅት ማድረግ ያስፈልገናል?
አስፋፊዎች የሚያደርጉት ዝግጅት
ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ በሚደረገው ዘመቻ የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጁ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን፣ ዘመዶቻችሁን፣ አብረዋችሁ የሚማሩትን፣ የሥራ ባልደረቦቻችሁንና ሌሎች የምታውቋቸውን ሰዎች ስም በዝርዝር በመጻፍ ጋብዟቸው።
በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚነበቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብቧቸው፤ እንዲሁም አሰላስሉባቸው።
በመታሰቢያው በዓል ላይ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ።