ጴጥሮስና ዮሐንስ በ33 ዓ.ም. ለተከበረው ፋሲካ ሰገነቱን እያዘጋጁ
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለመታሰቢያው በዓል እየተዘጋጃችሁ ነው?
ኢየሱስ ያከበረው የመጨረሻ ፋሲካ በዓይነቱ ልዩ ነበር። የሚሞትበት ጊዜ ስለተቃረበ ከሐዋርያቱ ጋር ፋሲካን መብላት እንዲሁም አዲስ ዓመታዊ በዓል ማለትም የጌታ ራትን ማቋቋም ፈልጎ ነበር። በመሆኑም በዓሉን የሚያከብሩበትን ቤት እንዲያዘጋጁ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። (ሉቃስ 22:7-13፤ ሽፋኑን ተመልከት።) ይህ ታሪክ መጋቢት 27 ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል መዘጋጀት እንዳለብን ያሳስበናል። ጉባኤዎች ከተናጋሪ፣ ከቂጣና ከወይን ጠጅ እንዲሁም ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ዝግጅት እንዳደረጉ ጥያቄ የለውም። ይሁንና በግለሰብ ደረጃ ለመታሰቢያው በዓል መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
ልባችሁን አዘጋጁ። የመታሰቢያውን በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አንብባችሁ አሰላስሉበት። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡ ፕሮግራም ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ ይገኛል። አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው ተጨማሪ መረጃ ለ12 ደግሞ ይበልጥ ዝርዝር የሆነ ፕሮግራም ይዟል። (በተጨማሪም የሚያዝያ 2020 የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦን ተመልከት።) ቤተሰቦች ቤዛው ስላለው ጥቅም በቤተሰብ አምልኳቸው ወቅት መወያየት ከፈለጉ የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮችን ተጠቅመው ጽሑፎች ማግኘት ይችላሉ።
ሌሎችን ጋብዙ። በመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ ላይ የተሟላ ተሳትፎ አድርጉ። ልትጋብዟቸው የምትችሏቸውን ሰዎች አስቡ፤ ለምሳሌ ተመላልሶ መጠየቆቻችሁን፣ የቀድሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን፣ የምታውቋቸውን ሰዎችና ዘመዶቻችሁን መጋበዝ ትችላላችሁ። ሽማግሌዎች የቀዘቀዙ አስፋፊዎችን መጋበዝ አለባቸው። የጋበዛችሁት ሰው የሚኖረው በአካባቢያችሁ ካልሆነ እሱ በሚኖርበት አካባቢ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ በjw.org መነሻ ገጽ አናት ላይ ያለውን ስለ እኛ የሚለውን ክፍል ተጫኑ፤ ከዚያም “የመታሰቢያው በዓል” የሚለውን ምረጡ።
ለመታሰቢያው በዓል ለመዘጋጀት ሌላስ ምን ማድረግ እንችላለን?