የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 መጋቢት ገጽ 8
  • ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለመታሰቢያው በዓል እየተዘጋጃችሁ ነው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የመታሰቢያውን በዓል የምናስተዋውቅበት ዘመቻ መጋቢት 17 ይጀምራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ በዓለም ዙሪያ ይሰራጫል!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • “ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 መጋቢት ገጽ 8
አንድ ወንድም የይሖዋ ምሥክር ላልሆነ ዘመዱ የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ሲሰጠው። ከበስተጀርባ ሚስቶቻቸው እየተጨዋወቱና ምግብ እያዘጋጁ ነው።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?

በክልላችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከእኛ ጋር የመታሰቢያውን በዓል እንዲያከብሩ ለመጋበዝ በየዓመቱ ለየት ያለ ጥረት እናደርጋለን። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አብዛኞቹን አናውቃቸውም። ሆኖም የምናውቃቸውን ሰዎችም መጋበዝ ይኖርብናል። ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያውቁት ሰው ከጋበዛቸው በስብሰባው ላይ የመገኘት አጋጣሚያቸው በጣም ሰፊ ነው። (yb08-E 11 አን. 3፤ 14 አን. 1) ታዲያ አንተ እነማንን ልትጋብዝ ትችላለህ?

  • ዘመዶችህን

  • የሥራ ባልደረቦችህን ወይም አብረውህ የሚማሩትን

  • ጎረቤቶችህን

  • ተመላልሶ መጠየቆችህን ወይም ጥናቶችህን (እያስጠናሃቸው ያሉትንም ሆነ ጥናት ያቆሙትን)

በተጨማሪም ሽማግሌዎች የቀዘቀዙ ሰዎችን ለመጋበዝ ጥረት ያደርጋሉ። ልትጋብዘው ያሰብከው ሰው የሚኖረው አንተ ባለህበት አካባቢ ባይሆንስ? በjw.org መነሻ ገጽ ላይ የሚገኘውን ስለ እኛ የሚለውን ክፍል ከፍተህ “የመታሰቢያው በዓል” የሚለውን ጠቅ በማድረግ እሱ በሚኖርበት አካባቢ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ጊዜና ቦታ ማግኘት ትችላለህ። በዚህ ዓመት ለሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ስትዘጋጅ እነማንን መጋበዝ እንደምትችል በጥሞና አስብበት፤ ከዚያም ያሰብካቸውን ሰዎች ጋብዝ።

1. በሥራ ቦታው ያለ አንድ ወንድም እረፍት ሰዓቱ ላይ ሲመሠክር። 2. አንድ ወንድም ምግብ ቤት ውስጥ ለሚሠራ ሰው ቪዲዮ ሲያሳይ።
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ