የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“በዓለማችን ላይ ካሉት ችግሮች መካከል አንዱን ማስወገድ ቢችሉ ኖሮ የትኛውን ያስወግዱ ነበር? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አምላክ ይህንም ሆነ ሌሎች ችግሮችን በቅርቡ እንደሚያስወግድ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [ለተጠቀሰው ችግር የሚስማማ ጥቅስ ምረጥ፤ ለምሳሌ ዳንኤል 2:44ን፣ ምሳሌ 2:21, 22ን፣ ማቴዎስ 7:21-23ን ወይም 2 ጴጥሮስ 3:7ን መጠቀም ይቻላል።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ በምድር ላይ እነዚህን አስደሳች ለውጦች የሚያመጣው መቼና እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት
“ሁሉም ሰው የተመቻቸ መኖሪያ ቤት የሚያገኝበትና ከድህነት የሚላቀቅበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህን አስመልክቶ አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠውን ተስፋ እስቲ ላንብብልዎት። [ኢሳይያስ 65:21-22ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም አምላክ ይህንን ተስፋ የሚፈጽመው እንዴት እንደሆነና እኛም የበረከቱ ተካፋይ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”