ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 60-68
ጸሎት ሰሚ የሆነውን ይሖዋን አወድሱ
ለይሖዋ የገባችሁትን ቃል መፈጸም እንድትችሉ ጸልዩ
የገባነውን ቃል አስመልክቶ መጸለያችን ቃላችንን ለመጠበቅ ያደረግነውን ውሳኔ ያጠናክርልናል
ከምንም ነገር በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ራሳችንን ለይሖዋ ስንወስን የገባነው ቃል ነው
ሐና
በጸሎት አማካኝነት የልባችሁን አውጥታችሁ በመናገር በይሖዋ እንደምትተማመኑ አሳዩ
ትርጉም ያለው ጸሎት፣ የልብን አውጥቶ መጸለይን ይጨምራል
ስንጸልይ የምንፈልገውን ለይተን የምንጠቅስ ከሆነ ይሖዋ የሚሰጠንን መልስ ይበልጥ ማስተዋል እንችላለን
ኢየሱስ
ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች የሚያቀርቡትን ጸሎት ሁሉ ይሰማል
ይሖዋ “ሁሉም ዓይነት ሰዎች” እሱን ለማወቅና ፈቃዱን ለማድረግ ከልብ ጥረት እስካደረጉ ድረስ የሚያቀርቡትን ጸሎት ይሰማል
በማንኛው ጊዜ ወደ ይሖዋ መጸለይ እንችላለን
ቆርኔሌዎስ
በጸሎትህ ውስጥ ልታካትታቸው የምትፈልጋቸውን ጉዳዮች ጻፍ