የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 ነሐሴ ገጽ 8
  • እውነትን ማስተማር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነትን ማስተማር
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የውይይት ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መጽሔት ለማበርከት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • የመግቢያ ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 ነሐሴ ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እውነትን አስተምሩ

ከመስከረም ጀምሮ የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ “እውነትን አስተምሩ” የሚል አዲስ የአቀራረብ ናሙና ይዞ ይወጣል። ይህን አዲስ አቀራረብ ስንጠቀም ዓላማችን አንድ ጥያቄና ጥቅስ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ትምህርቶች ለሰዎች ማስተማር ነው።

ግለሰቡ ፍላጎት እንዳለው ካስተዋልን ጽሑፎችን በመስጠት ወይም በjw.org ላይ የወጣን አንድ ቪዲዮ በማሳየት ቀጥሎ የምንመጣበትን ጊዜ በጉጉት እንዲጠብቅ ማድረግ እንችላለን። በጀመርነው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይቱን ለመቀጠል በጥቂት ቀናት ውስጥ ተመልሰን መሄድ ይኖርብናል። ይህ አዲስ የአቀራረብ ናሙና እና የተማሪ ክፍሎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? (በአማርኛ አይገኝም) በተባለው መጽሐፍ ላይ በሚገኙ ርዕሶች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ ይህ መጽሐፍ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በሚባለው መጽሐፍ ላይ ተመሥርቶ ቀለል ባለ መንገድ የተዘጋጀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ወይም ጥናት ለመምራት የሚረዱ ተጨማሪ ሐሳቦችንና ጥቅሶችን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ላይ ማግኘት እንችላለን።

ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ አንድ ብቻ ነው። (ማቴ 7:13, 14) የተለያየ ሃይማኖትና አስተዳደግ ያላቸውን ሰዎች ስናነጋግር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በግለሰብ ደረጃ እንዲማርካቸው አድርገን ማቅረብ ይኖርብናል። (1ጢሞ 2:4) በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች ላይ ይበልጥ ውይይት ስናደርግ “የእውነትን ቃል በአግባቡ በመጠቀም” ረገድ ያለን ችሎታ ይበልጥ ይሻሻላል፤ ይህ ደግም ደስታችን እንዲጨምርና እውነትን በማስተማር ረገድ ስኬታማ እንድንሆን ይረዳናል።—2ጢሞ 2:15

አንድ ወንድም ለአንድ ወጣት ጥቅስ እያነበበለት

ይህን አዲስ አቀራረብ መጠቀም የምንችለው . . .

  • ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል

  • መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስንመሠክር

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስናስጀምር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ