በጣሊያን፣ ምሥራቹ ከቤት ወደ ቤት ሲሰበክ
የመግቢያ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ
ጥያቄ፦ አምላክ የፈጠረን እንድንሞት አድርጎ ነው?
ጥቅስ፦ ራእይ 21:4
አበርክት፦ ይህ መጠበቂያ ግንብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትንና ሞትን አስመልክቶ ምን እንደሚናገር ያብራራል።
እውነትን አስተምሩ
መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው?
አበርክት፦ የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ያስጠናሉ፤ በጥናቱ ወቅት፣ ‘መከራ የበዛው ለምንድን ነው? ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረኝ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?’ እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይቻላል። ይህ አጭር ቪዲዮ መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት እንደሆነ ያሳያል። [መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።] በዚህ ጽሑፍ ተጠቅመን መወያየት እንችላለን። [ለማስጠናት ከምንጠቀምባቸው ጽሑፎች አንዱን አሳይ፤ ከተቻለ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚመራ አሳይ።]
የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።