የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 መጋቢት ገጽ 5
  • አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎች አምላክን እንዲሰሙ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ሰዎች አምላክ የሚፈልግባቸውን እንዲማሩ ለመርዳት የተዘጋጀ አዲስ መሣሪያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን ጽሑፍ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 መጋቢት ገጽ 5

ክርስቲያናዊ ሕይወት

አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር መጠቀም

አምላክን ስማ

አምላክን ስማ የተባለው ብሮሹር የተዘጋጀው በደንብ ማንበብ የማይችሉ ሰዎች ሥዕሎችን በማየት መሠረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን እንዲያውቁ ለመርዳት ታስቦ ነው። ሁለት ገጽ የሚይዘው እያንዳንዱ ትምህርት በጥንቃቄ ታስቦባቸው የተዘጋጁ ሥዕሎችን ይዟል፤ ከሥዕሎቹ አጠገብ የሚገኙት ቀስቶች በሥዕሎቹ ላይ የምትወያዩበትን ቅደም ተከተል ይጠቁሟችኋል።

አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ የተባለው ብሮሹር አምላክን ስማ ከተባለው ብሮሹር ጋር ተመሳሳይ ሥዕሎች ቢኖሩትም ተጨማሪ ጽሑፍ አለው፤ በመሆኑም የተሻለ የማንበብ ችሎታ ያላቸውን ጥናቶች ለማስጠናት ልንጠቀምበት እንችላለን። አንዳንድ አስፋፊዎች ጥናት በሚመሩበት ወቅት፣ ጥናታቸው አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር እነሱ ደግሞ አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ የተባለውን ብሮሹር መጠቀማቸው የተሻለ እንደሆነ አስተውለዋል። በአብዛኞቹ ገጾች ላይ የተማሪውን ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ልትወያዩባቸው የምትችሉ ተጨማሪ መረጃ የያዙ ሣጥኖች ይገኛሉ።

አንዲት እህት ጥናቷ አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር እሷ ደግሞ አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ የተባለውን ብሮሹር ይዛ ጥናት ስታስጠና

በወሩ ውስጥ የሚበረከተው ጽሑፍ ሌላ ቢሆንም እንኳ እነዚህን ብሮሹሮች ልታበረክቱ ትችላላችሁ። ጥናት ስትመሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ለማብራራት በሥዕላዊ መግለጫዎቹ ተጠቀሙ። ተማሪው በጥናቱ ወቅት ተሳትፎ እንዲያደርግ ለማበረታታት እንዲሁም ትምህርቱ ገብቶት እንደሆነ ለማወቅ ጥያቄዎችን ጠይቁ። በእያንዳንዱ ገጽ ግርጌ ላይ ያሉትን ጥቅሶች አንብባችሁ ተወያዩባቸው። ተማሪው ብሮሹሩን አጥንቶ ሲጨርስ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ መቀጠል ትችላላችሁ፤ ይህም ተማሪው እድገት አድርጎ እንዲጠመቅ ይረዳዋል።

አምላክን ስማ ከተባለው ብሮሹር ላይ አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት ስለነበራቸው ሕይወት ተማር
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ